የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ie ገጽ 21
  • የምንሞተው ለምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የምንሞተው ለምንድን ነው?
  • ስንሞት ምን እንሆናለን?
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አለመታዘዝ ሞት አስከተለ
  • “ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ”
  • የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • ኢየሱስ ያድናል—እንዴት?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
ስንሞት ምን እንሆናለን?
ie ገጽ 21

የምንሞተው ለምንድን ነው?

“በተራሮች ጫፍ ላይ ፀጥታ ሰፍኗል፤ ዛፎች ሁሉ ረጭ ብለዋል፤ ወፎች በየዛፎች ላይ ተኝተዋል:- ጠብቅ፤ አንተም አንድ ቀን እንዲሁ ፀጥ ትላለህ።”​—⁠ጆሃን ቮልፍጋንግ ቮን ጎተ፣ ጀርመናዊ ባለ ቅኔ

1, 2. (ሀ) ሰዎች ሲፈጠሩ ምን ዓይነት ፍላጎት በውስጣቸው ተቀርጿል? (ለ) የመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ባልና ሚስት ምን ዓይነት ሕይወት ነበራቸው?

አምላክ ሰዎችን ሲፈጥር ለዘላለም የመኖር ጉጉት በውስጣቸው ቀርጿል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “ዘላለማዊነትንም በሰው ልቦና አሳድሯል” ይላል። (መክብብ 3:​11 የ1980 ትርጉም) ሆኖም አምላክ ለሰው ልጆች የሰጠው ለዘላለም የመኖር ፍላጎት ብቻ አይደለም። ለዘላለም መኖር የሚችሉበትም አጋጣሚ ሰጥቷል።

2 የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የሆኑት አዳምና ሔዋን ምንም ዓይነት አእምሯዊም ሆነ አካላዊ ጉድለት ሳይኖራቸው ፍጹም ሆነው ነበር የተፈጠሩት። (ዘዳግም 32:​4) እስቲ አስበው፣ ምንም ዓይነት ሥር የሰደደ ሕመምም ሆነ ምንም ዓይነት ስጋትና ጭንቀት አልነበረባቸውም! ከዚህም በተጨማሪ አምላክ ውብ በሆነ ገነት ውስጥ እንዲኖሩ አድርጎ ነበር። አምላክ የሰው ልጅ ለዘላለም እንዲኖርና ውሎ አድሮም ምድር ፍጹም በሆኑ ዘሮቹ እንዲሞሉ ዓላማ ነበረው። (ዘፍጥረት 1:​31፤ 2:​15) ታዲያ የምንሞተው ለምንድን ነው?

አለመታዘዝ ሞት አስከተለ

3. የአዳምና የሔዋን ዘላለማዊ ሕይወት በምን ላይ የተመካ ነበር?

3 አምላክ አዳምን እንዲህ ሲል አዝዞት ነበር:- “ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” (ዘፍጥረት 2:​16, 17) ስለዚህ የአዳምና የሔዋን ዘላለማዊ ሕይወት አምላክን በመታዘዛቸው ላይ የተመካ ነበር።

4. አዳምና ሔዋን ኃጢአት ሲሠሩ በገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን አጋጣሚ ያጡት ለምንድን ነው?

4 የሚያሳዝነው፣ አዳምና ሔዋን አምላክ የሰጣቸውን ሕግ ጣሱ። (ዘፍጥረት 3:​1-6) እንዲህ በማድረጋቸውም ኃጢአተኞች ሆኑ፤ ምክንያቱም “ኃጢአት ዓመፅ ነው።” (1 ዮሐንስ 3:​4) በዚህም ምክንያት አዳምና ሔዋን ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን አጋጣሚ አጡ። ለምን? ምክንያቱም “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው።” (ሮሜ 6:​23) በመሆኑም አምላክ በአዳምና በሔዋን ላይ “አፈር ነህና፣ ወደ አፈርም ትመለሳለህ” የሚል ፍርድ በይኗል። ከዚያ በኋላ የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ገነት ከነበረው መኖሪያቸው ተባረሩ። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ዕለት የማያቋርጠውን አዝጋሚ የሞት ሂደት ተያያዙት።​—⁠ዘፍጥረት 3:​19, 23, 24

“ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ”

5. ሞት ለሰው ሁሉ የደረሰው እንዴት ነው?

5 ከዚህ በኋላ ኃጢአት በአዳምና በሔዋን በራሂዎች (genes) ውስጥ ሥር ሰደደ። በመሆኑም የሆነ ጉድለት ያለው ቅርጽ ማውጫ የተሟላ ቅርጽ ማውጣት እንደማይችል ሁሉ እነሱም ፍጹም የሆኑ ልጆች መውለድ አልቻሉም። (ኢዮብ 14:​4) የሚወለደው ሰው ሁሉ የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን ፍጹም የሆነ ጤናና የዘላለም ሕይወት ከማጣታቸውም በላይ ለዘሮቻቸውም ይህን ማውረስ እንዳልቻሉ ያረጋግጥልናል። ክርስቲያኑ ሐዋርያ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፣ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ።”​—⁠ሮሜ 5:​12፤ ከመዝሙር 51:​5 ጋር አወዳድር።

6. የምንሞተው ለምንድን ነው?

6 በዛሬው ጊዜ የሳይንስ ሊቃውንት የሰው ልጆች የሚያረጁትና የሚሞቱት ለምን እንደሆነ አያውቁም። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የምንሞተው ኃጢአትን ከመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ወላጆቻችን ስለ ወረስንና ኃጢአተኞች ሆነን ስለምንወለድ እንደሆነ ይገልጻል። ሆኖም ስንሞት ምን እንሆናለን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ