የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • gf ትምህርት 4 ገጽ 6-7
  • ስለ አምላክ መማር የምትችልበት መንገድ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስለ አምላክ መማር የምትችልበት መንገድ
  • የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እውነተኛው አምላክ ማን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • ከሚወደን አምላክ የተላከ ደብዳቤ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • አምላክ ማን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • አምላክ የሚባለው ማን ነው?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
ለተጨማሪ መረጃ
የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
gf ትምህርት 4 ገጽ 6-7

ትምህርት 4

ስለ አምላክ መማር የምትችልበት መንገድ

መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ስለ ይሖዋ መማር ትችላለህ። ከረጅም ጊዜ በፊት አምላክ የተወሰኑ ሰዎችን መርጦ የእርሱን ሐሳቦች በጽሑፍ እንዲያሰፍሩ አደረገ። እነዚህ ጽሑፎች መጽሐፍ ቅዱስ ተብለው ይጠራሉ። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ስለ አምላክ መማር እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ የይሖዋን ቃል ወይም መልእክት የያዘ በመሆኑ የአምላክ ቃል ተብሎም ይጠራል። ይሖዋ ፈጽሞ ስለማይዋሽ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገራቸውን ነገሮች በሙሉ ማመን እንችላለን። ‘እግዚአብሔር ሊዋሽ አይችልም።’ (ዕብራውያን 6:17, 18) የአምላክ ቃል እውነትን ይዟል።—ዮሐንስ 17:17

አንድ ቤተሰብ መጽሐፍ ቅዱስን አብሮ ሲያነብ

አምላክ ከሰጠን ውድ ስጦታዎች መካከል አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አንድ አፍቃሪ አባት ለልጁ ከሚልከው ደብዳቤ ጋር ይመሳሰላል። አምላክ ምድርን ወደ ገነትነት ለውጦ ግሩም መኖሪያ ቦታ ለማድረግ ያለውን ዓላማ ይነግረናል። ባለፉት ጊዜያት ያደረጋቸውን፣ አሁን እያደረገ ያለውንና ወደፊት ለታማኝ ልጆቹ የሚያደርግላቸውን ነገሮች ይነግረናል። በተጨማሪም ለሚገጥሙን ችግሮች መፍትሔ እንድናገኝና ደስተኞች እንድንሆን ይረዳናል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17

የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክ ወዳጆች ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን እንድትገነዘብ ይረዱሃል። መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት እንደምትፈልግ ብቻ ንገራቸው። ለዚህ ገንዘብ አያስከፍሉህም። (ማቴዎስ 10:8) ከዚህም በተጨማሪ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ትችላለህ። እነዚህ ስብሰባዎች የሚካሄዱት የመንግሥት አዳራሽ ተብለው በሚጠሩ የአምልኮ ቦታዎች ነው። በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ የምትገኝ ከሆነ ስለ አምላክ ባለህ እውቀት ረገድ ፈጣን ዕድገት ታደርጋለህ።

ከፈጠራቸው ነገሮች ስለ አምላክ መማር ትችላለህ። ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” ይላል። (ዘፍጥረት 1:1) ይሖዋ “ሰማይን” በፈጠረ ጊዜ ፀሐይንም አብሮ ሠራ። ይህ ስለ አምላክ ምን ይነግረናል? ይሖዋ ታላቅ ኃይል እንዳለው ይነግረናል። እንደ ፀሐይ ያለ ኃይል ያለው አካል ሊፈጥር የሚችለው እርሱ ብቻ ነው። በተጨማሪም ሙቀትና ብርሃን የምትሰጠውን እንዲሁም ፈጽሞ ተቃጥላ የማታልቀውን ፀሐይን መፍጠር ጥበብ የሚጠይቅ ስለሆነ ይሖዋ ጥበበኛ መሆኑን ይነግረናል።

ይሖዋ የፈጠራቸው ነገሮች እንደሚወደን ያሳያሉ። በምድር ላይ ስላሉት የተለያዩ ፍራፍሬዎች አስብ። ይሖዋ አንድ ዓይነት ፍሬ ብቻ ሊሰጠን ወይም ጭራሹኑ ምንም ፍሬ ላይሰጠን ይችል ነበር። ከዚያ ይልቅ ይሖዋ የተለያየ ቅርጽ፣ መጠን፣ ቀለምና ጣዕም ያላቸው ብዙ ዓይነት ፍራፍሬዎችን ሰጥቶናል። ይህም ይሖዋ አፍቃሪ ብቻ ሳይሆን በጣም ለጋስ፣ አሳቢና ደግ መሆኑን ያሳያል።—መዝሙር 104:24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ