የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bh ገጽ 199-ገጽ 201 አን. 4
  • ኢየሱስ ክርስቶስ—አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ክርስቶስ—አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ
  • ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስለ መሲሑ የተነገሩት ትንቢቶች ኢየሱስ መሲሕ እንደሆነ ያረጋግጣሉ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የመሲሑን መምጣት ይጠባበቁ ነበር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ከአምላክ ለሚገኘው እውቀት ቁልፍ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
ለተጨማሪ መረጃ
ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
bh ገጽ 199-ገጽ 201 አን. 4

ተጨማሪ ክፍል

ኢየሱስ ክርስቶስ​—አስቀድሞ የተነገረለት መሲሕ

ይሖዋ አምላክ መሲሑን ለይተን ማወቅ እንድንችል ለመርዳት በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት የሰውን ዘር ነፃ እንደሚያወጣ የተነገረለት ይህ መሲሕ ስለሚወለድበት ሁኔታ፣ ስለ አገልግሎቱና ስለ አሟሟቱ ዝርዝር መረጃዎችን እንዲሰጡ በመንፈሱ አነሳስቷቸዋል። እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ተፈጽመዋል። ትንቢቶቹ በሚያስገርም ሁኔታ ትክክለኛ ከመሆናቸውም በላይ ዝርዝር መረጃዎችን የያዙ ናቸው። ይህን በምሳሌ ለማስረዳት መሲሑ ከሚወለድበት ሁኔታና ከልጅነት ዘመኑ ጋር የተያያዙ ክንውኖችን የሚገልጹ ጥቂት ትንቢቶችን እስቲ እንመልከት።

ነቢዩ ኢሳይያስ መሲሑ የንጉሥ ዳዊት ዘር እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሮ ነበር። (ኢሳይያስ 9:7) በእርግጥም ኢየሱስ የተወለደው ከዳዊት ዘር ነው።—ማቴዎስ 1:1, 6-17

ሚክያስ የተባለ ሌላ የአምላክ ነቢይ ይህ ልጅ ከጊዜ በኋላ ገዥ እንደሚሆንና ‘በቤተ ልሔም ኤፍራታ’ እንደሚወለድ ተንብዮአል። (ሚክያስ 5:2) ኢየሱስ በተወለደበት ዘመን በእስራኤል ቤተልሔም ተብለው የሚጠሩ ሁለት ከተሞች ነበሩ። አንደኛዋ ከተማ በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል ናዝሬት አጠገብ የምትገኝ ሲሆን ሌላዋ ደግሞ በይሁዳ ምድር ኢየሩሳሌም አቅራቢያ ትገኝ ነበር። ኢየሩሳሌም አቅራቢያ የምትገኘው ቤተልሔም ቀደም ሲል ኤፍራታ ትባል ነበር። ልክ አስቀድሞ እንደተተነበየው ኢየሱስ የተወለደው በዚህች ከተማ ነው!—ማቴዎስ 2:1

ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ደግሞ የአምላክ ልጅ ‘ከግብፅ እንደሚጠራ’ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር። ኢየሱስ ሕፃን ሳለ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር። ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ከግብፅ የተመለሰ በመሆኑ ትንቢቱ በትክክል ተፈጽሟል።—ሆሴዕ 11:1፤ ማቴዎስ 2:15

ገጽ 200 ላይ በሚገኘው ሰንጠረዥ ላይ “ትንቢት” በሚለው ርዕስ ሥር የተዘረዘሩት ጥቅሶች መሲሑን አስመልክተው የተነገሩ ዝርዝር መረጃዎችን ይዘዋል። እባክህ እነዚህን ጥቅሶች “ፍጻሜ” በሚል ርዕስ ሥር ከሰፈሩት ጥቅሶች ጋር አመሳክር። ይህን ማድረግህ በአምላክ ቃል እውነተኝነት ላይ ያለህን እምነት ይበልጥ ያጠናክርልሃል።

እነዚህን ጥቅሶች ስታነብ ትንቢቶቹ የተጻፉት ኢየሱስ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት መሆኑን አስታውስ። ኢየሱስ “በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል” ሲል ተናግሯል። (ሉቃስ 24:44) በራስህ መጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እንደምትችለው በትንቢቶቹ ላይ የተጠቀሰው እያንዳንዱ ዝርዝር መግለጫ በትክክል ተፈጽሟል!

ስለ መሲሑ የተነገሩ ትንቢቶች

ክንውን

ትንቢት

ፍጻሜ

ከይሁዳ ነገድ ተወለደ

ዘፍጥረት 49:10

ሉቃስ 3:23-33

ከድንግል ተወለደ

ኢሳይያስ 7:14

ማቴዎስ 1:18-25

ከንጉሥ ዳዊት ዘር ተወለደ

ኢሳይያስ 9:7

ማቴዎስ 1:1, 6-17

ይሖዋ ልጁ መሆኑን አስታወቀ

መዝሙር 2:7

ማቴዎስ 3:17

ብዙዎች አላመኑበትም

ኢሳይያስ 53:1

ዮሐንስ 12:37, 38

በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ

ዘካርያስ 9:9

ማቴዎስ 21:1-9

የቅርብ ጓደኛው አሳልፎ ሰጠው

መዝሙር 41:9

ዮሐንስ 13:18, 21-30

በ30 ብር አሳልፎ ሰጠው

ዘካርያስ 11:12

ማቴዎስ 26:14-16

በከሳሾቹ ፊት ዝም አለ

ኢሳይያስ 53:7

ማቴዎስ 27:11-14

በልብሱ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ

መዝሙር 22:18

ማቴዎስ 27:35

በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ሳለ ተሳለቁበት

መዝሙር 22:7, 8

ማቴዎስ 27:39-43

ከአጥንቶቹ መካከል አንዱም አልተሰበረም

መዝሙር 34:20

ዮሐንስ 19:33, 36

ከባለጠጎች ጋር ተቀበረ

ኢሳይያስ 53:9

ማቴዎስ 27:57-60

ሳይበሰብስ ተነሳ

መዝሙር 16:10

የሐዋርያት ሥራ 2:24, 27

በአምላክ ቀኝ ተቀመጠ

መዝሙር 110:1

የሐዋርያት ሥራ 7:56

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ