መዝሙር 98
የመንግሥቱን ዘር መዝራት
በወረቀት የሚታተመው
1. ነፍሳቹን ለሱ የሰጣችሁ፣
የይሖዋ ባሮች ሁሉ፣
ወደ ጌታችን ሥራ ውጡ።
የሱን ፈለግ ተከተሉ።
በሚያፈሩ ልቦች ላይ በድፍረት
የእውነትን ዘር ብትዘሩ፣
ጥሩ ፍሬ ማፍራት ትችላላችሁ፤
መስኩ ላይ በትጋት ብትሠሩ።
2. ከዘራችሁት ዘር አንዳንዱ፣
ዓለት ልብ ላይ ይወድቃል።
ለጊዜው ፍላጎት ቢያሳዩም
የልባቸው ይገለጣል።
እሾህ ቃሉን ሲያንቀው፣ ሀብትን ሲሹ
ይህን ዓለም ይመርጣሉ።
በመልካም አፈር ላይ ከወደቀ ግን
ጥሩ ፍሬ ያፈራል ቃሉ።
3. ስኬት ማግኘታችሁ ’ሚመካው
ባብዛኛው በ’ናንተ ላይ ነው።
ፍቅር፣ ት’ግሥት እናሳያቸው፤
ምላሽ እንዲሰጥ ልባቸው።
በዘዴና በድፍረት እርዷቸው፤
እንዲጠፋ ፍርሃታቸው።
ያኔ መቶ እጥፍ ባይሆን ሠላሳ፣
ታጭዳላችሁ የልፋት ካሳ።
(በተጨማሪም ማቴ. 13:19-23፤ 22:37ን ተመልከት።)