መዝሙር 9
ይሖዋ አምላካችንን አወድሱ!
በወረቀት የሚታተመው
1. ይወደስ! ይሖዋ አምላክ!
ክብራማው ስሙም ይታወቅ!
ተናገር ቀኑ መቅረቡን፤
ሰዎች ሁሉ ይስሙ ጥሪውን!
ልጁ ’ሚገዛበት ጊዜ ደርሷል፤
ይሖዋ ራሱ ተናግሯል።
’ሚመጣውን በረከት በሙሉ፣
ተናገር ለሰዎች ሁሉ።
(አዝማች)
ይወደስ! ይሖዋ አምላክ!
ታላቅነቱን ዓለም ይወቅ!
2. ይወደስ! እልል በሉለት!
ስሙንም ከፍ አድርጉለት!
ምስጋና ሞልቶት ልባችን፣
ያወድሰው አንደበታችን።
ኃያል አምላክ ቢሆንም ትሑት ነው፤
ጥሩነቱ ወደር የለው።
ደግነት፣ ምሕረት፣ ፍቅር ያሳያል፤
ጩኸታችንን ይሰማል።
(አዝማች)
ይወደስ! ይሖዋ አምላክ!
ታላቅነቱን ዓለም ይወቅ!
(በተጨማሪም መዝ. 89:27፤ 105:1ን እና ኤር. 33:11ን ተመልከት።)