መዝሙር 63
ምንጊዜም ታማኝ መሆን
በወረቀት የሚታተመው
1. ለይሖዋ ታማኝ መሆን
ከልብ እንፈልጋለን፤
የሱ ንብረት ስለሆንን
እንታዘዘዋለን።
ምክሮቹ ስለሚበጁን
በተግባር ’ናውላቸው።
እሱ ታማኝ ስለሆነ
አንፈልግም ልንርቀው።
2. ለወንድሞች ታማኝ ’ንሁን፤
ሁሌም ’ንድረስላቸው።
አሳቢነት፣ ደግነትን
በተግባር ’ናሳያቸው።
ወንድሞችን፣ እህቶችን
ከልብ እናክብራቸው።
ቃሉ ይበልጥ ያቀራርበን፤
መቼም አንለያቸው።
3. ለተሾሙ ውድ ወንድሞች
ታማኝነት እናሳይ፤
ለሚሰጡን አመራርም
እንታዘዝ ሳንዘገይ።
ይሖዋ ይባርከናል፤
እኛም እንበረታለን።
ለይሖዋ ታማኝ ከሆን
ንብረቱ እንሆናለን።