መዝሙር 15
ፍጥረት የይሖዋን ክብር ይናገራል
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 19)
1. ይሖዋ ሆይ፣ ሳየው ፍጥረትህን፣
ያውጃሉ ከዋክብት ክብርህን።
ቀንና ሌት ቃልም ባያወጡ፣
ለትሑታን እውቀት ይገልጣሉ።
ቀንና ሌት ቃልም ባያወጡ፣
ለትሑታን እውቀት ይገልጣሉ።
2. አንተ ፈጠርክ ፀሐይ ከዋክብትን፤
ለባሕሩም አበጀህ ድንበሩን።
ላስተዋለው የሰማዩን ውበት፣
ሰውን ማሰብህ ድንቅ ነው በ’ውነት።
ላስተዋለው የሰማዩን ውበት፣
ሰውን ማሰብህ ድንቅ ነው በ’ውነት።
3. ሕግህ ፍጹም ት’ዛዞችህ እውነት፤
ታሳስበናለህ ዕለት ተ’ለት።
የ’ውነት ቃልህ ጥበብን ሰጥቶናል፤
ከጠራ ወርቅ እጅግ ይመረጣል።
የ’ውነት ቃልህ ጥበብን ሰጥቶናል፤
ከጠራ ወርቅ እጅግ ይመረጣል።