መዝሙር 16
የአምላክን መንግሥት ተገን አድርጉ!
በወረቀት የሚታተመው
1. እናንት የዋሆች፣ ፈልጉ ይሖዋን፤
ዛሬውኑ ጽድቅና ትሕትናን።
ከሚመጣው አስፈሪ የቁጣ ቀን፣
ተሰውራችሁ ለመዳን።
(አዝማች)
ያምላክን መንግሥት ተገን አድርጉ፤
ለአምላክ ታማኝ ሁኑ።
ጥበቃ፣ በረከት ታገኛላችሁ፤
ታዛዦች ከሆናችሁ።
2. ኑ እውነትና ፍትሕ የራባችሁ፤
ከ’ንግዲህ ለምን ታለቅሳላችሁ?
ለክርስቶስ ሥልጣን ከተገዛችሁ፣
ነፃነት ታገኛላችሁ።
(አዝማች)
ያምላክን መንግሥት ተገን አድርጉ፤
ለአምላክ ታማኝ ሁኑ።
ጥበቃ፣ በረከት ታገኛላችሁ፤
ታዛዦች ከሆናችሁ።
3. በደስታ ቀና አ’ርጉ ራሳችሁን፤
ተመልከቱ መንግሥቱ መቅረቡን።
የይሖዋን ብርሃንም ተቀበሉ፤
ካለሱ ሌላ አትፍሩ!
(አዝማች)
ያምላክን መንግሥት ተገን አድርጉ፤
ለአምላክ ታማኝ ሁኑ።
ጥበቃ፣ በረከት ታገኛላችሁ፤
ታዛዦች ከሆናችሁ።
(በተጨማሪም መዝ. 59:16ን፣ ምሳሌ 18:10ን እና 1 ቆሮ. 16:13ን ተመልከት።)