መዝሙር 113
ለአምላክ ቃል አመስጋኝ መሆን
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ አባት ሆይ፣ ደርሶናል ቃልህ፤
ማመስገን እንሻለን ለስጦታህ።
በመንፈስህ በመምራት አጻፍክ ሐሳብህን፤
በቃልህ ተመራን፤ ከአንተ ተማርን።
2. ቃልህን አስጻፍከው ’ንዲገባን ለኛ።
ነቢያት ሰዎች ነበሩ ልክ እንደኛ።
ከነሱ ’ንማራለን እምነትና ድፍረት።
ቃልህ ያነቃቃል፤ ይሰጣል ብርታት።
3. ወደ ልብ ይዘልቃል ቃልህ አለው ኃይል፤
መንፈስና ነፍስ እንኳ ይለያያል።
የልብን ሐሳብና ዝንባሌ ያውቃል፤
ተግሣጽና ጥበብ ይለግሰናል።
(በተጨማሪም መዝ. 119:16, 162ን፣ 2 ጢሞ. 3:16ን፣ ያዕ. 5:17ን እና 2 ጴጥ. 1:21ን ተመልከት።)