መዝሙር 122
እልፍ አእላፋት ወንድሞች
በወረቀት የሚታተመው
1. እልፍ አእላፋት ወንድሞች፣
ታማኝ ምሥክሮች፣
ጸንተዋል ባቋማቸው፤
እጅግ ብዙ ናቸው።
እልፍ አእላፍ ሆነናል፤
በቁጥር በዝተናል።
ብሔር፣ ቋንቋ፣ ነገድ ሳይለየን
ያህን ’ናከብራለን።
2. እልፍ አእላፋት ወንድሞች፣
የትም እንሰብካለን፤
ምሥራች ’ናበስራለን፣
ሰው ’ሚጓጓለትን።
መመሥከር አናቆምም፣
ውጥረት ቢሰማንም፤
ኢየሱስ ለዛሉ ሰላምን፣
ይሰጣል እፎይታን።
3. እልፍ አእላፍ ወንድሞችን፣
አምላክ ይጠብቃል፤
ቀን ከሌት በመቅደሱ
ያገለግሉታል።
እልፍ አእላፍ ሆነናል፤
እንመሠክራለን፤
በምድራዊው አደባባይ ላይ
አብረነው ’ንሠራለን።