የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rk ክፍል 6 ገጽ 15-17
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
  • እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው ገነት የምትገኘው የት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የኤደን ገነት ጉዳይ አንተንም ይነካል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ምድር ገነት ትሆናለች የሚለው ሐሳብ ቅዠት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
ለተጨማሪ መረጃ
እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
rk ክፍል 6 ገጽ 15-17

ክፍል 6

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

አምላክ ምድርን የፈጠራት ለሰው ልጆች ተስማሚ መኖሪያ እንድትሆን ነው። ቃሉ “ሰማያት የይሖዋ ናቸው፤ ምድርን ግን ለሰው ልጆች ሰጣት” በማለት ይናገራል።​—⁠መዝሙር 115:​16

አምላክ የመጀመሪያውን ሰው አዳምን ከመፍጠሩ በፊት ምድር ላይ ኤደን ተብሎ የሚጠራ አንድ ትንሽ ቦታ መርጦ ስፍራውን ውብ የአትክልት ቦታ አደረገው። ቅዱሳን መጻሕፍት፣ ከኤደን የሚመነጩ አራት ወንዞች እንደነበሩ ይናገራሉ።a የኤደን የአትክልት ሥፍራ ይገኝ የነበረው በአሁኗ ቱርክ ምሥራቃዊ ግዛት ውስጥ እንደሆነ ይታሰባል። ኤደን ገነት በእርግጥም በምድር ላይ ነበረ!

አምላክ አዳምን (አደምን) ከፈጠረ በኋላ “እንዲያለማውና እንዲንከባከበው በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው።” (ዘፍጥረት 2:​15) ቆየት ብሎም አምላክ ለአዳም ሚስት እንድትሆነው ሔዋንን ፈጠረለት። አምላክ ባልና ሚስቱን “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም” በማለት አዘዛቸው። (ዘፍጥረት 1:​28) ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው አምላክ ‘ምድርን መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ አልፈጠራትም።’​—⁠ኢሳይያስ 45:​18

አዳምና ሔዋን ግን ሆን ብለው ሕጉን በመጣስ በአምላክ ላይ ዓመፁ። በመሆኑም አምላክ ከኤደን ገነት አስወጣቸው። የሰው ልጆች በገነት ውስጥ የመኖር አጋጣሚያቸውን አጡ። የአዳም ኃጢአት ያስከተለው መዘዝ በዚህ ብቻ አላበቃም። ቅዱሳን መጻሕፍት እንዲህ ይላሉ፦ “በአንድ ሰው አማካኝነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፤ በኃጢአትም ምክንያት ሞት መጣ፤ ሁሉም ኃጢአት ስለሠሩም ሞት ለሰው ሁሉ ተዳረሰ።”​—⁠ሮም 5:​12

ታዲያ ይሖዋ፣ ምድር ገነት ሆና ደስተኛ በሆኑ ሰዎች እንድትሞላ ለማድረግ የነበረውን ዓላማ ትቶታል ማለት ነው? በፍጹም! አምላክ እንደሚከተለው በማለት ተናግሯል፦ ‘ከአፌ የሚወጣው ቃሌ ደስ የሚያሰኘኝን ነገር ያደርጋል፤ የተላከበትንም ዓላማ በእርግጥ ይፈጽማል እንጂ ያላንዳች ውጤት ወደ እኔ አይመለስም።’ (ኢሳይያስ 55:​11) በእርግጥም ምድር እንደገና ገነት ትሆናለች!

በገነት ውስጥ የሚኖረን ሕይወት ምን ይመስል ይሆን? በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የተገለጹትን ተስፋዎች በቀጣዮቹ ሁለት ገጾች ላይ ተመልከት።

a ዘፍጥረት 2:​10-14 እንዲህ ይላል፦ “የአትክልቱን ስፍራ የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ወጥቶ ይፈስ ነበር፤ ከዚያም ተከፋፍሎ አራት ወንዝ ሆነ። የመጀመሪያው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ . . . የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ . . . የሦስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ ይህ ወንዝ ከአሦር በስተ ምሥራቅ የሚፈስ ነው። አራተኛው ወንዝ ደግሞ ኤፍራጥስ ነው።”

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  •  አምላክ ለምድርና ለሰው ልጆች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

  •  አምላክ ይህን ዓላማውን እንደሚፈጽም እንዴት እናውቃለን?

ገነት ውስጥ ያሉ ሰዎች

ምድር ገነት ስትሆን . . .

የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ፦ ‘በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ ድምፁን ሰምተው ይወጣሉ።’​—⁠ዮሐንስ 5:​28, 29

እርጅና፣ በሽታ ወይም ሞት አይኖርም፦ “በዚያም የሚቀመጥ ማንኛውም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ አይልም።” (ኢሳይያስ 33:​24) አምላክ “እንባን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም፤ ሐዘንም ሆነ ጩኸት እንዲሁም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም።”​—⁠ራእይ 21:4

የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራል፦ “ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች፤ አምላክ፣ አዎ፣ አምላካችን ይባርከናል።”​—⁠መዝሙር 67:6

ሰዎች ጥሩ መኖሪያና አርኪ ሥራ ይኖራቸዋል፦ “ቤቶችን ይሠራሉ፤ በዚያም ይኖራሉ፤ . . . የመረጥኳቸው አገልጋዮቼም በእጃቸው ሥራ የተሟላ እርካታ ያገኛሉ።”​—⁠ኢሳይያስ 65:​21, 22

ጦርነት፣ ወንጀል ወይም ዓመፅ አይኖርም፦ ይሖዋ “ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።” (መዝሙር 46:⁠9) “ክፉዎች . . . ከምድር ገጽ ይጠፋሉ።”​—⁠ምሳሌ 2:​22

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ