የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ll ክፍል 8 ገጽ 18-19
  • የኢየሱስ ሞት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የኢየሱስ ሞት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
  • አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ክፍል 8
    አምላክን ስማ
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ኢየሱስ ክርስቶስ ከአምላክ የተላከ ነበርን?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
ll ክፍል 8 ገጽ 18-19

ክፍል 8

የኢየሱስ ሞት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

ኢየሱስ እኛ ሕይወት እንድናገኝ ሲል ሞቶልናል። ዮሐንስ 3:16

ሴቶች ባዶ የሆነውን የኢየሱስ መቃብር ሲመለከቱ

ኢየሱስ ከሞተ ከሦስት ቀናት በኋላ አንዳንድ ሴቶች መቃብሩን ለማየት በሄዱ ጊዜ ባዶ ሆኖ አገኙት። ይሖዋ ኢየሱስን ከሞት አስነስቶት ነበር።

ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ሲገለጥ፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ሰማይ ሲያርግ

በኋላም ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ተገለጠላቸው።

አዎ፣ ይሖዋ ኢየሱስን ኃያልና የማይሞት መንፈሳዊ ፍጡር አድርጎ ከሞት አስነስቶታል። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ ሰማይ ሲያርግ ተመልክተውታል።

  • የኃጢአት “ደሞዝ” ምንድን ነው?—ሮም 6:23

  • ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ በር ከፍቶልናል።—ሮም 5:21

አምላክ ኢየሱስን ከሞት አስነስቶ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ አደረገው። ዳንኤል 7:13, 14

ኢየሱስ በሰማይ ካለው ዙፋኑ ሆኖ ገነት በሆነችው ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎችን ሲያስተዳድር

ኢየሱስ ለሰው ልጆች ቤዛ ለመክፈል ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል። (ማቴዎስ 20:28) አምላክ በቤዛው አማካኝነት ለዘላለም መኖር የምንችልበትን አጋጣሚ ከፍቶልናል።

ይሖዋ ኢየሱስን በምድር ላይ እንዲገዛ ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። ከሞት ተነስተው በሰማይ የሚኖሩ 144,000 ታማኝ ሰዎች ከእሱ ጋር ይነግሣሉ። ኢየሱስና 144,000ዎቹ ጽድቅ የሰፈነበትን ሰማያዊ መስተዳድር ይኸውም የአምላክን መንግሥት ይመሠርታሉ።—ራእይ 14:1-3

የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋታል። ጦርነት፣ ወንጀል፣ ድህነትና ረሃብ ይወገዳሉ። ሰዎች እውነተኛ ደስታ ያገኛሉ።—መዝሙር 145:16

  • የአምላክ መንግሥት ምን በረከቶች ያመጣል?—መዝሙር 72

  • የአምላክ መንግሥት እንዲመጣ መጸለይ ይኖርብናል።—ማቴዎስ 6:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ