ክፍል 12
ቤተሰብህ ደስተኛ እንዲሆን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?
ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ፍቅር ነው። ኤፌሶን 5:33
አምላክ ያወጣው የጋብቻ መመሪያ አንድ ወንድ ለአንዲት ሴት ብቻ መሆን እንዳለበት ይገልጻል።
አፍቃሪ የሆነ ባል ሚስቱን በርኅራኄ የሚይዛት ሲሆን ስሜቷንም ይረዳላታል።
ሚስት ከባሏ ጋር መተባበር ይኖርባታል።
ልጆች ወላጆቻቸውን መታዘዝ ይገባቸዋል።
ጭካኔ የተሞላበትና ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ከመፈጸም ይልቅ ደግና ታማኝ ሁን። ቆላስይስ 3:5, 8-10
የአምላክ ቃል ባል ሚስቱን እንደ ገዛ አካሉ መውደድ እንዳለበት፣ ሚስትም ለባሏ ጥልቅ አክብሮት ማሳየት እንደሚገባት ይገልጻል።
ከጋብቻ ውጪ የሚፈጸም የፆታ ግንኙነት ስህተት ነው። ከአንድ በላይ ማግባትም ቢሆን ስህተት ነው።
የይሖዋ ቃል ቤተሰቦች እንዴት ደስተኛ መሆን እንደሚችሉ ያስተምራል።