የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 14 ገጽ 30-31
  • መላዋን ምድር የሚገዛ መንግሥት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መላዋን ምድር የሚገዛ መንግሥት
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ ወዳጆች በገነት ውስጥ ይኖራሉ
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
  • አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
    አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?
  • ከሞት የሚነሱት እነማን ናቸው? የሚኖሩትስ የት ነው?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • መላዋን ምድር የሚለውጥ መንግሥት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 14 ገጽ 30-31
ኢየሱስ ክርስቶስ ገነት የሆነችውን ምድር ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ

ትምህርት 14

መላዋን ምድር የሚገዛ መንግሥት

ይህ መንግሥት የትኛው እንደሆነ መገመት ትችላለህ?— አዎ፣ የአምላክ መንግሥት ነው፤ ይህ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋታል። ስለዚህ መንግሥት ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?—

እያንዳንዱ መንግሥት መሪ ወይም ንጉሥ አለው። ንጉሡ በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ያስተዳድራል። የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ማን እንደሆነ ታውቃለህ?— ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የሚኖረው በሰማይ ሲሆን በቅርቡ በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ ይነግሣል። ኢየሱስ በመላዋ ምድር ላይ ሲነግሥ ደስተኛ የምንሆን ይመስልሃል?—

በገነት ውስጥ ለማግኘት የምትጓጓው ነገር ምንድን ነው?

በጣም ደስተኞች እንደምንሆን የታወቀ ነው! በገነት ውስጥ ሰዎች እርስ በርስ አይጣሉም፤ ጦርነትም አይኖርም። ሁሉም ሰው እርስ በርስ ይዋደዳል። የሚታመም ወይም የሚሞት ሰው አይኖርም። ማየት የተሳናቸው ሰዎች ያያሉ፣ መስማት የማይችሉ ሰዎች ጆሮ ይከፈታል እንዲሁም አንካሳው መሮጥና መዝለል ይችላል። ሁሉም ሰው በቂ ምግብ ያገኛል። እንስሳት እርስ በርሳቸውም ሆነ ከእኛ ጋር በሰላም ይኖራሉ። የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ። በዚህ ብሮሹር ላይ ታሪካቸውን የተማርካቸው ብዙዎቹ ሰዎች ለምሳሌ ርብቃ፣ ረዓብ፣ ዳዊትና ኤልያስ ከሞት ይነሳሉ! እነዚህ ሰዎች ከሞት ሲነሱ ልታገኛቸው ትፈልጋለህ?—

ይሖዋ ይወድሃል እንዲሁም ደስተኛ እንድትሆን ይፈልጋል። ስለ ይሖዋ መማርህንና እሱን መታዘዝህን ከቀጠልክ ውብ በሆነች ገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር ትችላለህ! እንዲህ ዓይነት ሕይወት ማግኘት አትፈልግም?​—

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • ኢሳይያስ 2:4፤ 11:6-9፤ 25:8፤ 33:24፤ 35:5, 6

  • ዮሐንስ 5:28, 29፤ 17:3

ጥያቄዎች፦

  • የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ማን ነው?

  • ኢየሱስ የሚገዛው እነማንን ነው?

  • ኢየሱስ ምድርን በሚገዛበት ወቅት ምን ዓይነት ሁኔታ ይኖራል?

  • በገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር ከፈለግክ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ