የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • hf ክፍል 1 ገጽ 3-5
  • ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ
  • ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • 1 ይሖዋ የሰጣችሁን የሥራ ድርሻ ተቀበሉ
  • 2 አንዳችሁ ለሌላው ስሜት ከልብ እንደምታስቡ አሳዩ
  • 3 አንድ እንደሆናችሁ አስታውሱ
  • የትዳር ጓደኛችሁን በአክብሮት መያዝ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ
    ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
  • ከሠርጋችሁ ቀን በኋላ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • ጋብቻ—ከአምላክ የተገኘ ስጦታ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
ለተጨማሪ መረጃ
ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል
hf ክፍል 1 ገጽ 3-5
አንድ ባልና ሚስት በሠርጋቸው ዕለት

ክፍል 1

ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ

‘ፈጣሪ ከመጀመሪያውም ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።’—ማቴዎስ 19:4

የመጀመሪያውን ትዳር የመሠረተው ይሖዋa አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ይሖዋ የመጀመሪያዋን ሴት ከፈጠረ በኋላ ‘ወደ አዳም አመጣት።’ አዳምም በጣም በመደሰቱ “እንግዲህ እሷ የአጥንቶቼ አጥንት፣ የሥጋዬም ሥጋ ናት” ብሎ ተናገረ። (ዘፍጥረት 2:22, 23) በዛሬው ጊዜም ይሖዋ ባለትዳሮች ደስተኛ እንዲሆኑ ይፈልጋል።

ትዳር ስትመሠርቱ የቤተሰብ ሕይወታችሁ ምንም እንከን የሌለበት እንደሚሆን ጠብቃችሁ ይሆናል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ከልብ የሚዋደዱ ባልና ሚስትም እንኳ አንዳንድ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 7:28) እናንተም በዚህ ብሮሹር ውስጥ የሚገኙትን የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች በሥራ ላይ ካዋላችሁ ትዳራችሁም ሆነ የቤተሰብ ሕይወታችሁ አስደሳች ይሆናል።b​—መዝሙር 19:8-11

1 ይሖዋ የሰጣችሁን የሥራ ድርሻ ተቀበሉ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ባል የቤተሰብ ራስ ነው።​—ኤፌሶን 5:23

ባል ከሆንክ፣ ይሖዋ ሚስትህን እንድትንከባከብ ይጠብቅብሃል። (1 ጴጥሮስ 3:7) ይሖዋ ሚስትህን የፈጠራት ለአንተ ረዳት ወይም ማሟያ እንድትሆን አድርጎ ሲሆን በአክብሮትና በፍቅር እንድትይዛት ይፈልጋል። (ዘፍጥረት 2:18) የእሷን ፍላጎት ከራስህ ለማስቀደም ፈቃደኛ እስከ መሆን ድረስ ሚስትህን በጥልቅ ልትወድዳት ይገባል።—ኤፌሶን 5:25-29

ሚስት ከሆንሽ፣ ይሖዋ ባልሽን በጥልቅ እንድታከብሪና የሥራ ድርሻውን ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት እንድታግዢው ይጠብቅብሻል። (1 ቆሮንቶስ 11:3፤ ኤፌሶን 5:33) ባልሽ የሚያደርጋቸውን ውሳኔዎች ደግፊ፤ እንዲሁም በሙሉ ልብሽ ተባበሪው። (ቆላስይስ 3:18) እንዲህ ስታደርጊ በባልሽ እንዲሁም በይሖዋ ፊት ውብ ትሆኛለሽ።—1 ጴጥሮስ 3:1-6

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • የተሻላችሁ ባሎች ወይም ሚስቶች ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለባችሁ የትዳር ጓደኛችሁን ጠይቁ። ከዚያም በትኩረት አዳምጡ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ለማሻሻል፣ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ

  • ታጋሾች ሁኑ። አንዳችሁ ሌላውን ማስደሰት የምትችሉት እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ሁለታችሁም ብትሆኑ ጊዜ ያስፈልጋችኋል

2 አንዳችሁ ለሌላው ስሜት ከልብ እንደምታስቡ አሳዩ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ለትዳር ጓደኛችሁ ፍላጎት ትኩረት መስጠት ያስፈልጋችኋል። (ፊልጵስዩስ 2:3, 4) ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ “ለሰው ሁሉ ገር” እንዲሆኑ የሚፈልግ መሆኑን በማስታወስ የትዳር ጓደኛችሁን እንደ ውድ ንብረት አድርጋችሁ ተመልከቱ። (2 ጢሞቴዎስ 2:24) “ሳይታሰብበት የሚነገር ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤ የጥበበኞች ምላስ ግን ፈውስ ነው።” በመሆኑም የምትጠቀሙባቸውን ቃላት በጥንቃቄ ምረጡ። (ምሳሌ 12:18) አነጋገራችሁ ደግነትና ፍቅር የተላበሰ እንዲሆን የይሖዋ መንፈስ ይረዳችኋል።—ገላትያ 5:22, 23፤ ቆላስይስ 4:6

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ከበድ ባሉ ጉዳዮች ላይ መወያየት ከመጀመራችሁ በፊት ይሖዋ ተረጋግታችሁና አእምሯችሁን ክፍት አድርጋችሁ ለማዳመጥ እንዲረዳችሁ ጸልዩ

  • ምን እንደምትናገሩና እንዴት ብትናገሩት እንደሚሻል ቆም ብላችሁ አስቡ

3 አንድ እንደሆናችሁ አስታውሱ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ስታገባ ከትዳር ጓደኛህ ጋር “አንድ ሥጋ” ትሆናለህ። (ማቴዎስ 19:5) ይሁን እንጂ አሁንም ቢሆን ሁለት ግለሰቦች ስለሆናችሁ የተለያየ አመለካከት ሊኖራችሁ ይችላል። ስለዚህ አንድ ዓይነት አስተሳሰብና ስሜት ለማዳበር ጥረት ማድረግ ያስፈልጋችኋል። (ፊልጵስዩስ 2:2) ውሳኔዎች በምታደርጉበት ጊዜ አንድ መሆናችሁ በጣም አስፈላጊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “መመካከር ሲኖር የታቀደው ነገር ይሳካል” ይላል። (ምሳሌ 20:18) አንድ ላይ ሆናችሁ አስፈላጊ ውሳኔዎችን በምታደርጉበት ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ተመሩ።—ምሳሌ 8:32, 33

ባልና ሚስት ምንጊዜው ተባብረው ይሠራሉ፤ ልብስም ሆነ ዕቃ አንድ ላይ ያጥባሉ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ለትዳር ጓደኛችሁ አንዳንድ ሐሳቦችን ወይም አመለካከታችሁን ብቻ ሳይሆን ስሜታችሁንም ግለጹ

  • አንድ ነገር ለማድረግ ቃል ከመግባታችሁ በፊት የትዳር ጓደኛችሁን አማክሩ

a መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ የግል ስም ይሖዋ ነው።

b ለአጻጻፍ እንዲያመች ሲባል በዚህ ብሮሹር ላይ አንዳንድ ጊዜ በተባዕታይ ፆታ የተጠቀምን ቢሆንም የቀረቡት ነጥቦች ለሁለቱም ባለትዳሮች ይሠራሉ።

ምክንያታዊና አዎንታዊ ሁኑ

ከራሳችሁም ሆነ ከትዳር ጓደኛችሁ ፍጽምናን አትጠብቁ። (መዝሙር 103:14፤ ያዕቆብ 3:2) በትዳር ጓደኛችሁ ጥሩ ባሕርያት ላይ ትኩረት ለማድረግ ሞክሩ። የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን መከተል ጥቅም እንዳለው እምነት ይኑራችሁ፤ እንዲሁም ታጋሾች ሁኑ። (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ይሖዋ የእሱን ምክር ለመከተል የምታደርጉትን ጥረት ይባርከዋል፤ ዓመት አልፎ ዓመት ሲተካ ትዳራችሁ ይበልጥ እየጠነከረ ይሄዳል።—ገላትያ 6:9

ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦

  • የትዳር ጓደኛዬ፣ ከራሴ አስበልጬ እንደማስብላት ይሰማታል?

  • ለትዳር ጓደኛዬ ያለኝን ፍቅርና አክብሮት ለማሳየት በዛሬዋ ዕለት ምን አድርጌያለሁ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ