መዝሙር 143
በጨለማ ዓለም ውስጥ ብርሃን ማብራት
በወረቀት የሚታተመው
እነዚህ ጨለማ ቀናት
ባመፅ ተሞልተዋል።
ይታያል የተስፋ ብርሃን፤
በቅርቡ ይነጋል።
(አዝማች)
መል’ክታችን ብሩህ፣
በጨለማ ያበራል፤
ተስፋ፣ ብርሃን ይዟል።
እንደ ንጋት ጸዳል፣
ከጨለማው ባሻገር
ያሳየናል።
የተኙ ከ’ንቅልፍ ይነሱ፤
አልቋልና ጊዜው።
በተስፋው እናጽናናቸው፤
እንጸልይላቸው።
(አዝማች)
መል’ክታችን ብሩህ፣
በጨለማ ያበራል፤
ተስፋ፣ ብርሃን ይዟል።
እንደ ንጋት ጸዳል፣
ከጨለማው ባሻገር
ያሳየናል።
(በተጨማሪም ዮሐ. 3:19ን፣ 8:12ን፣ ሮም 13:11, 12ን እና 1 ጴጥ. 2:9ን ተመልከት።)