መዝሙር 153
ምን ይሰማሃል?
በወረቀት የሚታተመው
ስትሰብክ ምን ተሰማህ?
ሰዎችን ስታስተምር፣
ልባቸውን ለመንካት
ያቅምህን ስትጥር?
ምርጥህን ስትሰጠው
አምላክ ያሳካልሃል።
ልበ ቅን የሆኑትን
እሱ ያውቃቸዋል።
(አዝማች)
ደስ ይለናል መስጠታችን
ላምላክ ሁለንተናችንን።
ኑ! እናቅርብ የውዳሴ
መሥዋ’ት ሁልጊዜ።
ያኔ ምን ተሰማህ?
ቃሉን የነገርካቸው
እውነትን ሲቀበሉ
ተነክቶ ልባቸው?
አንዳንዶች ቢርቁም፣
ሌሎች ከ’ውነት ቢወጡም
በስብከቱ ሥራችን
መጽናት ነው ምርጫችን።
(አዝማች)
ደስ ይለናል መስጠታችን
ላምላክ ሁለንተናችንን።
ኑ! እናቅርብ የውዳሴ
መሥዋ’ት ሁልጊዜ።
ስታውቅ ምን ተሰማህ?
አምላክ እንደሚረዳህ፤
እንደሰጠህ ባደራ
የምትሠራው ሥራ?
ለዛ ባለው መንገድ
ግን በድፍረት እንስበክ፤
ሥራው በቅርብ ያበቃል፤
ቅኖችን እንፈልግ።
(አዝማች)
ደስ ይለናል መስጠታችን
ላምላክ ሁለንተናችንን።
ኑ! እናቅርብ የውዳሴ
መሥዋ’ት ሁልጊዜ።
(በተጨማሪም ሥራ 13:48ን፣ 1 ተሰ. 2:4ን እና 1 ጢሞ. 1:11ን ተመልከት።)