የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 6 ገጽ 20-ገጽ 21 አን. 8
  • ተስፋ የተሰጠበት ልጅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተስፋ የተሰጠበት ልጅ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተሰጠበት ልጅ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • “በልቧ ታሰላስል ነበር”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ማርያም ከተወችው ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 6 ገጽ 20-ገጽ 21 አን. 8
ስምዖን ሕፃኑን ኢየሱስን አቅፎት፤ ዮሴፍ፣ ማርያምና ነቢዪቱ ሐና አጠገቡ ሆነው ሲመለከቱት

ምዕራፍ 6

ተስፋ የተሰጠበት ልጅ

ሉቃስ 2:21-39

  • ኢየሱስ ተገረዘ፤ በኋላም ወደ ቤተ መቅደሱ ተወሰደ

ዮሴፍና ማርያም ወደ ናዝሬት ከመመለስ ይልቅ እዚያው ቤተልሔም ቆዩ። አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጠው ሕግ በሚያዘው መሠረት ኢየሱስ ስምንት ቀን ሲሞላው አስገረዙት። (ዘሌዋውያን 12:2, 3) ለአንድ ሕፃን በዚያው ቀን ስም ማውጣትም የተለመደ ነው። ስለዚህ መልአኩ ገብርኤል በነገራቸው መሠረት ልጃቸውን ኢየሱስ ብለው ጠሩት።

ይህ ከሆነ በኋላ ከአንድ ወር የሚበልጥ ጊዜ አለፈ፤ ኢየሱስም 40 ቀን ሞላው። ታዲያ በዚህ ጊዜ ወላጆቹ ወዴት ይወስዱታል? ካረፉበት ቦታ በስተ ሰሜን ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ወደሚገኘው በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መቅደስ ወሰዱት። በሕጉ መሠረት ወንድ ልጅ ከተወለደ ከ40 ቀናት በኋላ እናትየዋ ወደ ቤተ መቅደሱ ሄዳ የመንጻት መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርባታል።—ዘሌዋውያን 12:4-8

ማርያምም ያደረገችው ይህንኑ ነው። ለመሥዋዕት ይዛ የመጣችው ሁለት ትናንሽ ወፎችን ነው። ይህም የዮሴፍንና የማርያምን የኑሮ ደረጃ ይጠቁማል። ሕጉ እንደሚያዝዘው ለመሥዋዕት መቅረብ ያለበት የበግ ጠቦትና አንድ ወፍ ነው። ሆኖም እናቲቱ የበግ ጠቦት ለማቅረብ አቅሟ የማይፈቅድላት ከሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ማቅረብ ትችላለች። ማርያምም አቅሟ የፈቀደላትና ያቀረበችው ይህንን ነው።

“የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ”

ዮሴፍና ማርያም፣ የመንጻት መሥዋዕት ለማቅረብ ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው ወደ ቤተ መቅደሱ መጡ

እስራኤላውያን ሴቶች፣ ልጅ ሲወልዱ በሕጉ መሠረት ለተወሰነ ጊዜ ያህል ርኩስ እንደሆኑ ተደርገው ይቆጠራሉ። ይህ ጊዜ ሲያበቃ ለመንጻት ሲሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይህም ፍጽምና የጎደለውና ኃጢአተኛ የሆነ ልጅ መወለዱን እንዲያስታውሱ ያደርጋል። እርግጥ ሕፃኑ ኢየሱስ ፍጹምና ቅዱስ ነው። (ሉቃስ 1:35) ያም ቢሆን “የሚነጹበት ጊዜ ሲደርስ” ሕጉ በሚያዘው መሠረት ማርያምና ዮሴፍ ሕፃኑን ወደ ቤተ መቅደሱ “ይዘውት መጡ።”—ሉቃስ 2:22

በቤተ መቅደሱ ውስጥ አንድ በዕድሜ የገፋ ሰው ወደ ዮሴፍና ማርያም መጣ። ይህ ሰው ስምዖን ይባላል። ይሖዋ ተስፋ የሰጠበትን ክርስቶስ ወይም መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት አምላክ ለስምዖን ገልጦለት ነበር። ስምዖን በዚህ ዕለት ወደ ቤተ መቅደሱ እንዲመጣ መንፈስ ቅዱስ የመራው ሲሆን በዚያም ዮሴፍንና ማርያምን ከሕፃን ልጃቸው ጋር አገኛቸው። ስምዖን ሕፃኑን ተቀብሎ አቀፈው።

ከዚያም ኢየሱስን አቅፎ እንዲህ ሲል አምላክን አመሰገነ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ሆይ፣ በተናገርከው ቃል መሠረት አሁን ባሪያህን በሰላም እንዲያርፍ ታደርገዋለህ፤ ምክንያቱም ዓይኖቼ ሰዎችን የምታድንበትን መንገድ አይተዋል፤ ይህም በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፤ ደግሞም ብሔራትን የጋረደውን መሸፈኛ የሚገልጥ ብርሃን እንዲሁም የሕዝብህ የእስራኤል ክብር ነው።”—ሉቃስ 2:29-32

ዮሴፍና ማርያም ይህን ሲሰሙ ተደነቁ። ስምዖን እነሱንም ከባረካቸው በኋላ ለማርያም፣ ልጇ “በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅም ሆነ መነሳት ምክንያት” እንደሚሆን ነገራት፤ እንዲሁም ልክ እንደ ስለታም ሰይፍ ሐዘን በነፍሷ እንደሚያልፍ ገለጸላት።—ሉቃስ 2:34

በዚህ ዕለት በቤተ መቅደሱ አንዲት ሴትም ተገኝታለች። ይህች ሴት ሐና የምትባል የ84 ዓመት ነቢዪት ናት። ሐና ከቤተ መቅደስ ጠፍታ አታውቅም። በዚያ ወቅት ወደ ዮሴፍና ማርያም መጣች። ከዚያም አምላክን ማመስገንና ይሰሙ ለነበሩት ሰዎች ሁሉ ስለ ኢየሱስ መናገር ጀመረች።

ዮሴፍና ማርያም በቤተ መቅደሱ በተከናወኑት በእነዚህ ነገሮች ምን ያህል ተደስተው እንደሚሆን መገመት አያዳግትም! እነዚህ ነገሮች ልጃቸው፣ አምላክ ተስፋ የሰጠበት መሲሕ መሆኑን እንዳረጋገጡላቸው ምንም አያጠራጥርም።

  • በዘመኑ ልማድ መሠረት ለአንድ እስራኤላዊ ልጅ ስም የሚወጣለት መቼ ነው?

  • አንዲት እስራኤላዊት እናት ልጇ 40 ቀን ሲሞላው ምን ማድረግ ይጠበቅባታል? ማርያም ያደረገችው ነገር ስለ ኑሮዋ ምን ይጠቁመናል?

  • በቤተ መቅደሱ ውስጥ የኢየሱስን ማንነት የለዩት እነማን ናቸው? ይህንንስ ያሳዩት እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ