የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 7 ገጽ 22-ገጽ 23 አን. 6
  • ኮከብ ቆጣሪዎች ወደ ኢየሱስ መጡ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኮከብ ቆጣሪዎች ወደ ኢየሱስ መጡ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስና ኮከብ ቆጣሪዎቹ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • “ሰብአ ሰገል” እነማን ነበሩ? “ኮከቡን” ያዘጋጀው አምላክ ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • “ኮከቡን” የላከው ማን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ‘ጠቢባኑን’ ወደ ኢየሱስ የመራቸው ምን ዓይነት ኮከብ ነው?
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 7 ገጽ 22-ገጽ 23 አን. 6
ኮከብ ቆጣሪዎች አንድ ኮከብ ተከትለው ዮሴፍ፣ ማርያምና ኢየሱስ ወደሚኖሩበት ቤት ሲመጡ

ምዕራፍ 7

ኮከብ ቆጣሪዎች ወደ ኢየሱስ መጡ

ማቴዎስ 2:1-12

  • ኮከብ ቆጣሪዎች አንድን “ኮከብ” ተከትለው ወደ ኢየሩሳሌም ከዚያም ወደ ኢየሱስ ሄዱ

የተወሰኑ ሰዎች ከምሥራቅ መጡ። እነዚህ ሰዎች የከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት፣ በሰዎች ሕይወት ውስጥ የሚከሰቱ ነገሮች ያላቸውን ትርጉም እንደሚያውቁ የሚናገሩ ኮከብ ቆጣሪዎች ናቸው። (ኢሳይያስ 47:13) በምሥራቅ በሚገኘው አገራቸው ሳሉ የተመለከቱትን “ኮከብ” ተከትለው በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች ተጉዘዋል፤ “ኮከቡ” የመራቸው ግን ወደ ቤተልሔም ሳይሆን ወደ ኢየሩሳሌም ነው።

ኮከብ ቆጣሪዎቹ ኢየሩሳሌም ሲደርሱ “የተወለደው የአይሁዳውያን ንጉሥ የሚገኘው የት ነው? በምሥራቅ ሳለን ኮከቡን በማየታችን ልንሰግድለት መጥተናል” በማለት ጠየቁ።—ማቴዎስ 2:1, 2

ኮከብ ቆጣሪዎች ለንጉሥ ሄሮድስ ሲሰግዱ

ኢየሩሳሌም ያለው ንጉሥ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ በጣም ደነገጠ። ስለዚህ የካህናት አለቆችንና ሌሎች የሃይማኖት መሪዎችን ጠርቶ ክርስቶስ የሚወለደው የት እንደሆነ ጠየቃቸው። እነሱም ቅዱሳን መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ “በቤተልሔም” እንደሆነ ነገሩት። (ማቴዎስ 2:5፤ ሚክያስ 5:2) በዚህ ጊዜ ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹን በድብቅ አስጠርቶ “ሄዳችሁ ሕፃኑን በደንብ ፈልጉ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም ሄጄ እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ” አላቸው። (ማቴዎስ 2:8) ሆኖም ሄሮድስ ልጁን ለማግኘት የፈለገው ሊገድለው አስቦ ነው!

ኮከብ ቆጣሪዎቹ ከሄዱ በኋላ አንድ አስገራሚ ነገር ተፈጸመ። በምሥራቅ ሳሉ የተመለከቱት “ኮከብ” ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ጀመር። ይህ “ኮከብ” እነሱን ለመምራት የተዘጋጀ እንጂ ተራ ኮከብ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ኮከብ ቆጣሪዎቹ፣ “ኮከቡ” ዮሴፍና ማርያም ከትንሽ ልጃቸው ጋር ከሚኖሩበት ቤት በላይ እስኪቆም ድረስ ተከተሉት።

አንድ ኮከብ ተከትለው ወደ ቤተልሔም የመጡት ኮከብ ቆጣሪዎች ለማርያምና ለኢየሱስ ስጦታ ሲሰጡ

ኮከብ ቆጣሪዎቹ ቤቱ ውስጥ ሲገቡ ማርያምን ከትንሹ ኢየሱስ ጋር አገኟት። በዚህ ጊዜ ኮከብ ቆጣሪዎቹ ለኢየሱስ ሰገዱለት። ከዚያም ወርቅ፣ ነጭ ዕጣንና ከርቤ በስጦታ አበረከቱለት። በኋላ ላይ ወደ ሄሮድስ ሊሄዱ ሲሉ አምላክ ይህን እንዳያደርጉ በሕልም አስጠነቀቃቸው። በመሆኑም በሌላ መንገድ አድርገው ወደ አገራቸው ተመለሱ።

ኮከብ ቆጣሪዎቹን ሲመራ የነበረውን “ኮከብ” ያዘጋጀው ማን ይመስልሃል? “ኮከቡ” በቤተልሔም ወደነበረው ወደ ኢየሱስ በቀጥታ እንዳልመራቸው አስታውስ። ከዚህ ይልቅ የመራቸው ከንጉሥ ሄሮድስ ጋር ወደተገናኙበት ወደ ኢየሩሳሌም ነው፤ ሄሮድስ ደግሞ ኢየሱስን መግደል ፈለገ። ደግሞም ኢየሱስ የት እንዳለ ኮከብ ቆጣሪዎቹ ለሄሮድስ እንዳይነግሩት አምላክ ጣልቃ ገብቶ ባያስጠነቅቃቸው ኖሮ ሄሮድስ ኢየሱስን ከመግደል አይመለስም። በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ኢየሱስ እንዲገደል የፈለገው የአምላክ ጠላት የሆነው ሰይጣን ነው፤ ይህን ዓላማውን ለማሳካትም በዚህ ዘዴ ተጠቅሟል።

  • ኮከብ ቆጣሪዎቹ የተመለከቱት “ኮከብ” ተራ ኮከብ እንዳልሆነ እንዴት እናውቃለን?

  • ኮከብ ቆጣሪዎቹ ኢየሱስን ያገኙት የት ነው?

  • ኮከብ ቆጣሪዎቹን የመራቸው ሰይጣን ነው የምንለው ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ