የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 23 ገጽ 60-ገጽ 61 አን. 5
  • ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በቅፍርናሆም የተፈጸሙ ተጨማሪ ተአምራት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ምኩራቦች—ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የሰበኩባቸው ቦታዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • በገሊላ በስፋት ሰበከ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 23 ገጽ 60-ገጽ 61 አን. 5
የታመሙ ሰዎች በጴጥሮስ ቤት ተሰበሰቡ፤ ኢየሱስም ፈወሳቸው

ምዕራፍ 23

ኢየሱስ በቅፍርናሆም ታላላቅ ሥራዎችን አከናወነ

ማቴዎስ 8:14-17 ማርቆስ 1:21-34 ሉቃስ 4:31-41

  • ኢየሱስ ጋኔን አስወጣ

  • የጴጥሮስ አማት ተፈወሰች

ኢየሱስ አራት ደቀ መዛሙርቱን ይኸውም ጴጥሮስን፣ እንድርያስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ሰው አጥማጆች እንዲሆኑ ጋብዟቸዋል። ከዚያም በሰንበት ቀን ሁሉም በቅፍርናሆም ወደሚገኝ ምኩራብ ሄዱ። ኢየሱስ በምኩራቡ ውስጥ ማስተማር ጀመረ፤ እዚህም ባስተማረበት መንገድ ሕዝቡ ተገረሙ። ምክንያቱም የሚያስተምረው እንደ ጸሐፍት ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን ነው።

በዚህ የሰንበት ቀን ጋኔን የያዘው አንድ ሰው ምኩራቡ ውስጥ ተገኝቷል። ሰውየው እዚያው ምኩራቡ ውስጥ እንዲህ ብሎ በኃይል ጮኸ፦ “የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ እኛ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለን? የመጣኸው ልታጠፋን ነው? ማን እንደሆንክ በሚገባ አውቃለሁ፤ አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ ነህ!” ኢየሱስ ግን በሰውየው ላይ ያደረውን ጋኔን “ዝም በል፤ ከእሱም ውጣ!” ብሎ ገሠጸው።—ማርቆስ 1:24, 25

ርኩሱም መንፈስ ሰውየውን ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ሆኖም ሰውየውን “ምንም ሳይጎዳው ለቆት ወጣ።” (ሉቃስ 4:35) በምኩራቡ ውስጥ ያሉት ሰዎች በጣም ተገረሙ! “ይህ ምንድን ነው? . . . ርኩሳን መናፍስትን እንኳ ሳይቀር በሥልጣን ያዛል፤ እነሱም ይታዘዙለታል” ተባባሉ። (ማርቆስ 1:27) ስለዚህ አስገራሚ ክንውን የሚገልጽ ወሬ በመላዋ ገሊላ ተዳረሰ።

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከምኩራቡ ወጥተው ወደ ስምዖን (ወይም ጴጥሮስ) ቤት ሄዱ። እዚያም የጴጥሮስ አማት ኃይለኛ ትኩሳት ይዟት በጣም ታምማ አገኟት። በመሆኑም እንዲረዳት ኢየሱስን ለመኑት። ስለዚህ ኢየሱስ ወደ እሷ ሄደና እጇን ይዞ አስነሳት። ወዲያው ተፈወሰች፤ ከዚያም ኢየሱስንና ከእሱ ጋር ያሉ ደቀ መዛሙርቱን ማገልገል ምናልባትም ለእነሱ ምግብ ማዘጋጀት ጀመረች!

ፀሐይ ልትጠልቅ አካባቢ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ሰዎች ሕመምተኞቻቸውን እየያዙ ወደ ጴጥሮስ ቤት መጉረፍ ጀመሩ። ብዙም ሳይቆይ የከተማው ሰው ሁሉ ጴጥሮስ ደጃፍ ላይ ተሰበሰበ! ሰዎቹ የመጡት ለምንድን ነው? ፈውስ ፈልገው ነው። “ሰዎች በተለያየ በሽታ የተያዙ ሕመምተኞቻቸውን ወደ እሱ አመጡ። እሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።” (ሉቃስ 4:40) በሽታቸው ምንም ይሁን ምን ኢየሱስ በትንቢት በተነገረው መሠረት የታመሙትን ሁሉ ፈወሰ። (ኢሳይያስ 53:4) አጋንንትን እንኳ ከሰዎች አስወጣ። አጋንንቱ፣ ሰዎቹን ለቀው ሲወጡ “አንተ የአምላክ ልጅ ነህ” እያሉ ይጮኻሉ። (ሉቃስ 4:41) ኢየሱስ ግን የገሠጻቸው ሲሆን ከዚያ በኋላ እንዳይናገሩ ከለከላቸው። አጋንንቱ እሱ፣ ክርስቶስ እንደሆነ ያውቃሉ፤ ሆኖም እውነተኛውን አምላክ የሚያገለግሉ እንዲመስሉ አልፈለገም።

አጋንንት ያደረባቸው ሰዎች

አንድ ጋኔን ወይም ብዙ አጋንንት በአንድ ሰው ላይ ሲያድሩ በግለሰቡ ላይ ከፍተኛ ሥቃይ ሊያስከትሉ ይችላሉ። (ማቴዎስ 17:14-18) ግለሰቡ አጋንንቱ ከወጡለት በኋላ ግን አእምሯዊም ሆነ አካላዊ ጤንነቱ ይመለስለታል። ኢየሱስ በአምላክ ቅዱስ መንፈስ አማካኝነት አጋንንትን የማስወጣት ኃይል እንዳለው በተደጋጋሚ አሳይቷል።—ሉቃስ 8:39፤ 11:20

  • በቅፍርናሆም በሚገኝ ምኩራብ ውስጥ በሰንበት ቀን ምን ተከናወነ?

  • ኢየሱስ ከምኩራቡ ከወጣ በኋላ ወዴት ሄደ? እዚያስ ምን አደረገ?

  • የከተማዋ ሰዎች ኢየሱስ በዚያ ያደረገውን ሲመለከቱ ምን አሉ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ