የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 132 ገጽ 300-ገጽ 301 አን. 3
  • “ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር”
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ”
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • “በእውነትም የአምላክ ልጅ ነበር”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • የኢየሱስ ሰብዓዊ ሕይወት የመጨረሻ ዕለት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ማርያም የሐዘንን ሰይፍ ተቋቁማለች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 132 ገጽ 300-ገጽ 301 አን. 3
ኢየሱስ ከሁለት ወንጀለኞች ጋር በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ከሞተ በኋላ አንድ መኮንን “ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር” አለ

ምዕራፍ 132

“ይህ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር”

ማቴዎስ 27:45-56 ማርቆስ 15:33-41 ሉቃስ 23:44-49 ዮሐንስ 19:25-30

  • ኢየሱስ በእንጨት ላይ ተሰቅሎ ሞተ

  • ኢየሱስ ሲሞት የተፈጸሙ እንግዳ ክንውኖች

አሁን ከቀኑ “ስድስት ሰዓት” ሆኗል። “አገሩ በሙሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በጨለማ ተሸፈነ።” (ማርቆስ 15:33) እንግዳ የሆነውና ጭንቅ የሚለው ይህ ጨለማ የተከሰተው በፀሐይ ግርዶሽ ሳቢያ አይደለም። ምክንያቱም የፀሐይ ግርዶሽ የሚፈጠረው አዲስ ጨረቃ በምትኖርበት ጊዜ ነው፤ አሁን የፋሲካ ወቅት ሲሆን በዚህ ጊዜ ደግሞ ጨረቃ ሙሉ ነች። ከዚህም ሌላ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ከሚቆየው የፀሐይ ግርዶሽ በተለየ ይህ ጨለማ የቆየው ረዘም ላለ ጊዜ ነው። ስለዚህ ምድሪቱ በጨለማ እንድትሸፈን ያደረገው አምላክ ነው!

በኢየሱስ ላይ ሲያላግጡ የቆዩት ሰዎች በዚህ ወቅት ምን እንደሚሰማቸው አስበው። አካባቢው በጨለማ በተሸፈነበት ሰዓት አራት ሴቶች ወደ መከራ እንጨቱ ቀረቡ። እነሱም የኢየሱስ እናት፣ ሰሎሜ፣ መግደላዊቷ ማርያምና የትንሹ ያዕቆብ እናት የሆነችው ማርያም ናቸው።

ሐዋርያው ዮሐንስ በሐዘን ከተደቆሰችው የኢየሱስ እናት ጋር ሆኖ ‘በመከራው እንጨት አጠገብ’ ቆሟል። ማርያም ወልዳና ተንከባክባ ያሳደገችው ልጇ ተሰቅሎ ሲሠቃይ እየተመለከተች ነው። በዚህ ወቅት “ትልቅ ሰይፍ” በውስጧ ያለፈ ያህል ተሰምቷት መሆን አለበት። (ዮሐንስ 19:25፤ ሉቃስ 2:35) ኢየሱስ በከፍተኛ ሥቃይ ላይ ቢሆንም የእናቱ ነገር አሳስቦታል። እንደምንም ተጣጥሮ በጭንቅላቱ ወደ ዮሐንስ በማመልከት እናቱን “ልጅሽ ይኸውልሽ!” አላት። ከዚያም ወደ ማርያም በመጠቆም ዮሐንስን “እናትህ ይህችውልህ!” አለው።—ዮሐንስ 19:26, 27

በዚህ መንገድ ኢየሱስ፣ እናቱን እንዲንከባከባት ይበልጥ ለሚወደው ሐዋርያ በአደራ ሰጠው፤ በዚህ ወቅት ማርያም መበለት ሳትሆን አትቀርም። ኢየሱስ፣ ወንድሞቹ ይኸውም የማርያም ሌሎች ልጆች በእሱ ገና እንዳላመኑ ያውቃል። በመሆኑም የእናቱ ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ፍላጎትም እንዲሟላ ዝግጅት እያደረገ ነው። ይህ እንዴት ያለ ጥሩ ምሳሌ ነው!

ጨለማው ሊገፈፍ አካባቢ ኢየሱስ “ተጠማሁ” አለ። ይህን ሲል የቅዱስ መጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም እያደረገ ነው። (ዮሐንስ 19:28፤ መዝሙር 22:15) ኢየሱስ፣ ንጹሕ አቋሙ እስከ መጨረሻ ድረስ እንዲፈተን አባቱ ጥበቃውን ከእሱ ላይ እንዳነሳ ሆኖ ተሰምቶታል። ክርስቶስ “ኤሊ፣ ኤሊ፣ ላማ ሳባቅታኒ?” ብሎ ጮኸ፤ ትርጉሙም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው። ኢየሱስ የተናገረው በገሊላ በሚነገር የአረማይክ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። በአቅራቢያው የቆሙት ሰዎች ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ስላልሆነላቸው “አያችሁ! ኤልያስን እየተጣራ ነው” አሉ። ከመካከላቸው አንዱ ሮጦ በመሄድ የኮመጠጠ የወይን ጠጅ ውስጥ ሰፍነግ ከነከረ በኋላ በመቃ ላይ አድርጎ እንዲጠጣ ለኢየሱስ ሰጠው። ሌሎች ግን “ተዉት! እስቲ ኤልያስ መጥቶ ያወርደው እንደሆነ እንይ” አሉ።—ማርቆስ 15:34-36

ከዚያም ኢየሱስ “ተፈጸመ!” ብሎ ጮኸ። (ዮሐንስ 19:30) አዎን፣ አባቱ ወደ ምድር ሲልከው እንዲያከናውነው የሰጠውን ሥራ ሁሉ ፈጽሟል። በመጨረሻም ኢየሱስ “አባት ሆይ፣ መንፈሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ” አለ። (ሉቃስ 23:46) በዚህ መንገድ ኢየሱስ የሕይወቱን ኃይል ለይሖዋ ሰጠ፤ ይህን ያደረገው አምላክ እንደገና መልሶ እንደሚሰጠው እርግጠኛ ሆኖ ነው። ከዚያም ክርስቶስ በአምላክ ሙሉ በሙሉ በመተማመን ራሱን ዘንበል አድርጎ ሞተ።

በዚህ ጊዜ ኃይለኛ የምድር መናወጥ ተከሰተ፤ ዓለቶችም ተሰነጣጠቁ። የምድር መናወጡ በጣም ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ከኢየሩሳሌም ውጭ ያሉ መቃብሮች ተከፈቱ፤ አስከሬኖችም ከመቃብሩ ውስጥ ተስፈንጥረው ወጡ። በዚያ የሚያልፉ ሰዎች አስከሬኖቹን ሲያዩ ወደ “ቅድስቲቱ ከተማ” ገብተው የተመለከቱትን ነገር አወሩ።—ማቴዎስ 12:11፤ 27:51-53

ኢየሱስ ሲሞት፣ በአምላክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳኑ የሚለየው ትልቅና ወፍራም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተቀደደ። ይህ አስደናቂ ክንውን አምላክ፣ ልጁን በገደሉት ሰዎች ላይ የተሰማውን ቁጣ ይገልጻል፤ ከዚህም ሌላ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ማለትም ወደ ሰማይ የሚያስገባው መንገድ እንደተከፈተ ያመለክታል።—ዕብራውያን 9:2, 3፤ 10:19, 20

ሰዎቹ ታላቅ ፍርሃት ያደረባቸው መሆኑ የሚያስገርም አይደለም። ግድያውን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት የተሰጠው መኮንን “ይህ ሰው በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነበር” አለ። (ማርቆስ 15:39) ይህ መኮንን፣ በጲላጦስ ፊት በተካሄደው ችሎት ላይ ኢየሱስ የአምላክ ልጅ ስለ መሆኑ በተጠየቀበት ወቅት በቦታው ኖሮ ሊሆን ይችላል። አሁን ኢየሱስ ጻድቅ እንደሆነ አልፎ ተርፎም የአምላክ ልጅ እንደሆነ አመነ።

በእነዚህ ያልተለመዱ ክንውኖች ስሜታቸው የተጎዳ ሌሎች ሰዎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘንና ኀፍረት ለመግለጽ “ደረታቸውን እየደቁ ወደ ቤታቸው ተመለሱ።” (ሉቃስ 23:48) በርቀት ሆነው ከሚመለከቱት መካከል አንዳንድ ጊዜ ከኢየሱስ ጋር ይጓዙ የነበሩ በርካታ ሴት ደቀ መዛሙርት ይገኙበታል። እነሱም በእነዚህ አስገራሚ ክንውኖች ስሜታቸው በጥልቅ ተነክቷል።

“ስቀለው”

የኢየሱስ ጠላቶች “ስቀለው!” በማለት ጮኸዋል። (ዮሐንስ 19:15) በወንጌል ዘገባዎች ላይ “እንጨትን” ለማመልከት የተሠራበት የግሪክኛ ቃል ስታውሮስ ነው። ሂስትሪ ኦቭ ዘ ክሮስ የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “ስታውሮስ፣ ገበሬዎች አጥር ለመሥራት መሬት ላይ እንደሚቸነክሩት ዓይነት ጠንካራና ‘ቀጥ ያለ’ እንጨትን ያመለክታል፤ ከዚህ የተለየ ትርጉም የለውም።”

  • ለሦስት ሰዓት ያህል የጨለመው በፀሐይ ግርዶሽ ምክንያት ሊሆን የማይችለው ለምንድን ነው?

  • ኢየሱስ በዕድሜ የገፉ ወላጆችን በመንከባከብ ረገድ ምን ግሩም ምሳሌ ትቷል?

  • የምድር ነውጡ ምን አስከተለ? የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ለሁለት መቀደዱ ምን ትርጉም አለው?

  • የኢየሱስ ሞትና ከዚያ ጋር ተያይዘው የተፈጸሙት ክንውኖች በቦታው ያሉት ሰዎች ምን እንዲሰማቸው አደረጉ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ