የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • od ምዕ. 3 ገጽ 17-23
  • “በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ”
  • የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ ለይቶ ማወቅ
  • “በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ” የተባልነው ለምንድን ነው?
  • በይሖዋና በዝግጅቱ እንደምንተማመን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
  • “ታማኝና ልባም ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ‘ምንጊዜም በጉን ይከተሉታል’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ታማኝ እና ልባም የሆነ “ባሪያ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ታማኙ መጋቢና የበላይ አካሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
od ምዕ. 3 ገጽ 17-23

ምዕራፍ 3

“በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ”

ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈው በዕብራውያን 13:7 ላይ የሚገኘው ይህ ሐሳብ “የበላዮቻችሁን አስቡ” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። በ33 ዓ.ም. ከዋለው የጴንጤቆስጤ ዕለት ጀምሮ ታማኞቹ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት አዲስ ለተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ አመራር በመስጠት የበላይ አካል ሆነው የማስተዳደር ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል። (ሥራ 6:2-4) ይህ የበላይ አካል በቁጥር እያደገ ሄዶ በ49 ዓ.ም. ከኢየሱስ ሐዋርያት በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችን አካተተ። አከራካሪ በነበረው የግርዘት ጉዳይ ላይ ውሳኔ በተላለፈበት ወቅት የበላይ አካሉ ‘በኢየሩሳሌም የሚገኙ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን’ ያቀፈ ነበር። (ሥራ 15:1, 2) በተጨማሪም በየትኛውም ቦታ ከሚገኙ ክርስቲያኖች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የማየት ኃላፊነት ነበረበት። ደብዳቤዎችንና ድንጋጌዎችን ይልክ የነበረ ሲሆን ይህም ጉባኤዎቹ እንዲጠናከሩ እንዲሁም ደቀ መዛሙርቱ በሐሳብም ሆነ በተግባር አንድነት እንዲኖራቸው አስችሏል። ጉባኤዎቹ የበላይ አካሉ ለሚሰጠው አመራር ይታዘዙና ይገዙ ነበር። ይህም የይሖዋን በረከት አስገኝቶላቸዋል፤ እድገት እንዲያደርጉም አስችሏቸዋል።—ሥራ 8:1, 14, 15፤ 15:22-31፤ 16:4, 5፤ ዕብ. 13:17

2 ሁሉም ሐዋርያት ከሞቱ በኋላ ታላቅ ክህደት ብቅ ማለት ጀመረ። (2 ተሰ. 2:3-12) ኢየሱስ ስለ ስንዴውና ስለ እንክርዳዱ በተናገረው ምሳሌ ላይ በትንቢት እንደገለጸው ስንዴው (ቅቡዓን ክርስቲያኖች) በእንክርዳድ (በአስመሳይ ክርስቲያኖች) ተወርሶ ነበር። ከዚያ በኋላ ባሉት ዘመናት ሁሉ፣ የመከር ወቅት እስኪደርስ ይኸውም “[እስከዚህ] ሥርዓት መደምደሚያ” ድረስ ሁለቱም ቡድኖች አብረው እንዲያድጉ ተትተዋል። (ማቴ. 13:24-30, 36-43) በዚያ ወቅት፣ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በግለሰብ ደረጃ በኢየሱስ ዘንድ ተቀባይነት ነበራቸው። ሆኖም በወቅቱ የበላይ አካል አልነበረም፤ እንዲሁም ኢየሱስ ለተከታዮቹ አመራር የሚሰጥበት መስመር በግልጽ አይታወቅም ነበር። (ማቴ. 28:20) ይሁን እንጂ ኢየሱስ በመከር ወቅት ለውጥ እንደሚመጣ ተንብዮአል።

3 “ታማኝና ልባም ባሪያ በእርግጥ ማን ነው?” ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ጥያቄ ያነሳው ትንቢታዊ ትርጉም ያዘለ አንድ ምሳሌ በተናገረበት ወቅት ነው፤ ይህ ምሳሌ ኢየሱስ የዚህን “ሥርዓት መደምደሚያ” አስመልክቶ የተናገረው ‘ምልክት’ ክፍል ነው። (ማቴ. 24:3, 42-47) ኢየሱስ ታማኙ ባሪያ ለአምላክ ሕዝቦች “በተገቢው ጊዜ” መንፈሳዊ ምግብ በማቅረቡ ሥራ እንደሚጠመድ ጠቁሟል። ኢየሱስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን አመራር ይሰጥ የነበረው በአንድ ግለሰብ ሳይሆን በቡድን በሚሠሩ የተወሰኑ ወንዶች አማካኝነት ነበር፤ በዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ላይ የሚጠቀምበት ታማኝ ባሪያም አንድ ሰው ብቻ ሊሆን አይችልም።

‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ ለይቶ ማወቅ

4 ኢየሱስ፣ ተከታዮቹን የመመገብ ኃላፊነት የሰጠው ለማን ነው? ይህን ኃላፊነት እንዲወጡ በምድር ላይ ያሉ የተቀቡ ክርስቲያኖችን መጠቀሙ ተገቢ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ቅቡዓን ክርስቲያኖችን “ንጉሣዊ ካህናት” ብሎ የሚጠራቸው ሲሆን ‘ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራቸውን የእሱን ድንቅ ባሕርያት በየቦታው እንዲያውጁ’ ተልዕኮ የተሰጣቸው መሆኑን ይገልጻል። (1 ጴጥ. 2:9፤ ሚል. 2:7፤ ራእይ 12:17) በምድር ላይ የሚገኙ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በሙሉ የታማኙ ባሪያ ክፍል ናቸው? አይደሉም። ኢየሱስ ሴቶችና ልጆች ሳይቆጠሩ 5,000 ለሚያህሉ ወንዶች በተአምር ሥጋዊ ምግብ አቅርቦ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ምግቡን ለደቀ መዛሙርቱ ከሰጠ በኋላ ለሕዝቡ እንዲያከፋፍሉ አደረገ። (ማቴ. 14:19) በጥቂቶች ተጠቅሞ ብዙኃኑን መግቧል። በዛሬው ጊዜም መንፈሳዊ ምግብ የሚያቀርበው በተመሳሳይ መንገድ ነው።

5 ስለዚህ “ታማኝና ልባም መጋቢ” ሆነው የሚያገለግሉት ክርስቶስ በሚገኝበት ወቅት መንፈሳዊ ምግብ በማዘጋጀቱም ሆነ በማከፋፈሉ ሥራ በቀጥታ የሚሳተፉ እንዲሁም በቡድን የሚሠሩ በመንፈስ የተቀቡ ጥቂት ወንድሞች ናቸው። (ሉቃስ 12:42) “ታማኝና ልባም ባሪያ” ሆነው የሚያገለግሉት ወንድሞች መጨረሻዎቹ ቀናት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ በዋናው መሥሪያ ቤት አብረው ሲሠሩ ቆይተዋል። በዛሬው ጊዜ፣ እነዚህ የተቀቡ ወንድሞች የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል ናቸው።

6 ክርስቶስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን ፍጻሜ የሚገልጽ ትምህርት ለማውጣትና የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት እንደሆነ የሚጠቁም ወቅታዊ መመሪያ ለመስጠት የበላይ አካሉን መሣሪያ አድርጎ ይጠቀምበታል። ይህ መንፈሳዊ ምግብ በየአካባቢው በሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች አማካኝነት ይሰራጫል። (ኢሳ. 43:10፤ ገላ. 6:16) በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን አንድ እምነት የሚጣልበት ባሪያ ወይም መጋቢ ቤቱን የማስተዳደር ኃላፊነት ነበረው። በተመሳሳይም ታማኝና ልባም ባሪያ የእምነት ቤተሰቡን የማስተዳደር ኃላፊነት ተጥሎበታል። በመሆኑም ታማኙ ባሪያ ቁሳዊ ንብረቶችን፣ የስብከቱን ሥራ፣ የወረዳና የክልል ስብሰባ ፕሮግራሞችን፣ በድርጅቱ ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሚያገለግሉ የበላይ ተመልካቾችን ሹመት እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን ዝግጅት በበላይነት ይቆጣጠራል፤ ይህ ሁሉ ሥራ የሚከናወነው ‘ለቤተሰቦቹ’ ጥቅም ነው።—ማቴ. 24:45

7 ለመሆኑ “ቤተሰቦቹ” እነማን ናቸው? በአጭር አነጋገር፣ ምግቡን የሚመገቡት ናቸው። መጀመሪያ ላይ የቤተሰቡ አባላት በሙሉ የተቀቡ ክርስቲያኖች ነበሩ። በኋላም ‘የሌሎች በጎች’ ክፍል የሆኑት እጅግ ብዙ ሕዝብ የቤተሰቡ ክፍል ሆኑ። (ዮሐ. 10:16) ሁለቱም ቡድኖች ታማኙ ባሪያ የሚያቀርበውን መንፈሳዊ ምግብ ይመገባሉ።

8 ኢየሱስ በዚህ ሥርዓት ላይ ፍርድ ለማስተላለፍና የቅጣት እርምጃ ለመውሰድ በሚመጣበት በታላቁ መከራ ወቅት ታማኙን ባሪያ “በንብረቱ ሁሉ ላይ ይሾመዋል።” (ማቴ. 24:46, 47) የታማኙ ባሪያ አባላት በሰማይ ሽልማታቸውን ያገኛሉ። ከሌሎቹ የ144,000 አባላት ጋር በሰማይ ከክርስቶስ ጋር አብረው ይገዛሉ። በዚያን ወቅት በምድር ላይ ታማኝና ልባም ባሪያ ባይኖርም ይሖዋና ኢየሱስ በምድር ላይ ላሉ የመሲሐዊው መንግሥት ዜጎች መመሪያ የሚያስተላልፉት “መኳንንት” ሆነው እንዲያገለግሉ በሚሾሙት ሰዎች አማካኝነት ይሆናል።—መዝ. 45:16

“በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ” የተባልነው ለምንድን ነው?

9 ‘በመካከላችን ሆነው አመራር የሚሰጡትን የምናስብበትና’ በእነሱ ላይ እምነት እንዳለን የምናሳይበት ብዙ ምክንያት አለን። እንዲህ ማድረጋችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፦ “ተግተው ስለሚጠብቋችሁና ይህን በተመለከተ ስሌት ስለሚያቀርቡ በመካከላችሁ ሆነው አመራር ለሚሰጧችሁ ታዘዙ እንዲሁም ተገዙ፤ ይህን የምታደርጉት ሥራቸውን በደስታ እንጂ በሐዘን እንዳያከናውኑ ነው፤ አለዚያ ሥራቸውን የሚያከናውኑት በሐዘን ይሆናል፤ ይህ ደግሞ እናንተን ይጎዳችኋል።” (ዕብ. 13:17) መንፈሳዊ ጥበቃ ስለሚያደርጉልንና ለመንፈሳዊ ደህንነታችን ስለሚያስቡ አመራር የሚሰጡንን መታዘዛችንና ለእነሱ መገዛታችን ወሳኝ ነገር ነው።

10 በአንደኛ ቆሮንቶስ 16:14 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው ጳውሎስ “የምታደርጉትን ነገር ሁሉ በፍቅር አድርጉ” ብሏል። ከአምላክ ሕዝቦች ጋር በተያያዘ የሚደረጉ ውሳኔዎች ከሁሉ በላቀው የፍቅር ባሕርይ ላይ የተመሠረቱ ናቸው። አንደኛ ቆሮንቶስ 13:4-8 ስለ ፍቅር ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይቀናም። ጉራ አይነዛም፣ አይታበይም፣ ጨዋነት የጎደለው ምግባር አያሳይም፣ የራሱን ፍላጎት አያስቀድምም፣ በቀላሉ አይበሳጭም። ፍቅር የበደል መዝገብ የለውም። ፍቅር በዓመፅ አይደሰትም፤ ከዚህ ይልቅ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል። ሁሉን ችሎ ያልፋል፣ ሁሉን ያምናል፣ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፣ ሁሉን ነገር በጽናት ይቋቋማል። ፍቅር ለዘላለም ይኖራል።” ለይሖዋ አገልጋዮች ጥቅም ሲባል የሚደረጉ ውሳኔዎች በሙሉ በፍቅር ላይ የተመሠረቱ በመሆናቸው እንዲህ ባለው አመራር ላይ እምነት የምንጥልበት በቂ ምክንያት አለን። ደግሞም ይህ የይሖዋ ፍቅር መገለጫ ነው።

ለመንፈሳዊ ደህንነታችን ለሚያስቡት ወንድሞች መገዛታችን ወሳኝ ነገር ነው

11 በመጀመሪያው መቶ ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም ይሖዋ ሕዝቡን ለመምራት የሚጠቀመው ፍጽምና በሚጎድላቸው ሰዎች ነው። ቀደም ባሉት ዘመናትም ይሖዋ ፈቃዱን ለማስፈጸም የተጠቀመው ፍጽምና በጎደላቸው ሰዎች ነበር። ኖኅ መርከብ ሠርቷል፤ እንዲሁም በዘመኑ ስለሚመጣው ጥፋት ሰብኳል። (ዘፍ. 6:13, 14, 22፤ 2 ጴጥ. 2:5) ሙሴ ደግሞ የይሖዋን ሕዝብ ከግብፅ ምድር እየመራ እንዲያወጣ ተሹሞ ነበር። (ዘፀ. 3:10) መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ መሪነት የጻፉት ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎች ናቸው። (2 ጢሞ. 3:16፤ 2 ጴጥ. 1:21) በመሆኑም ይሖዋ በዛሬው ጊዜ የስብከቱንና ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ ለመምራት ፍጽምና በጎደላቸው ሰዎች መጠቀሙ በአምላክ ድርጅት ላይ ያለንን እምነት አያዳክመውም። ከዚህ ይልቅ ድርጅቱ፣ የይሖዋ ድጋፍ ባይኖረው ኖሮ አሁን እያከናወነ ያለውን ነገር መፈጸም እንደማይችል ስለምናውቅ እምነታችን ይጠነክራል። ታማኙ ባሪያ ከባድ መከራ ቢደርስበትም በርካታ ነገሮችን ማከናወን መቻሉ የአምላክ መንፈስ አመራር እንዳልተለየው ያረጋግጣል። በዛሬው ጊዜ ይሖዋ በድርጅቱ ምድራዊ ክፍል ላይ የተትረፈረፈ በረከት እያፈሰሰ ነው። በመሆኑም ይህን ድርጅት በሙሉ ልባችን እንደግፋለን፤ እንዲሁም በድርጅቱ እንተማመናለን።

በይሖዋና በዝግጅቱ እንደምንተማመን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

12 በጉባኤ ውስጥ በኃላፊነት ቦታ ላይ የተሾሙ ወንድሞች ሹመታቸው ያስከተለባቸውን ግዴታ በደስታ በመቀበልና ይህን ግዴታቸውን በታማኝነት በመወጣት በይሖዋና በዝግጅቱ እንደሚተማመኑ ያሳያሉ። (ሥራ 20:28) የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች እንደመሆናችን መጠን ከቤት ወደ ቤት በቅንዓት እናገለግላለን፣ ተመላልሶ መጠየቅ እናደርጋለን እንዲሁም የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንመራለን። (ማቴ. 24:14፤ 28:19, 20) ታማኙ ባሪያ ከሚያቀርበው የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ ሙሉ በሙሉ መጠቀም እንድንችል ትላልቅ ስብሰባዎችን ጨምሮ ለሁሉም ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች በሚገባ እንዘጋጃለን፤ በስብሰባዎቹም ላይ አዘውትረን እንገኛለን። በእነዚህ ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ ከወንድሞቻችን ጋር በመቀራረብ የምናገኘው ማበረታቻ በእጅጉ ይጠቅመናል።—ዕብ. 10:24, 25

13 ድርጅቱን በቁሳዊ መዋጮ መደገፋችን በድርጅቱ እንደምንተማመን ያሳያል። (ምሳሌ 3:9, 10) ወንድሞቻችን ቁሳዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ስናውቅ አፋጣኝ ምላሽ እንሰጣለን። (ገላ. 6:10፤ 1 ጢሞ. 6:18) ይህን የምናደርገው በወንድማማች ፍቅር ተገፋፍተን ነው፤ ከይሖዋና ከድርጅቱ ላገኘነው መልካም ነገር በምላሹ አድናቆት ማሳየት የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች ምንጊዜም በንቃት እንከታተላለን።—ዮሐ. 13:35

14 በድርጅቱ እንደምንተማመን የምናሳይበት ሌላው መንገድ ለሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ድጋፍ መስጠት ነው። ይህ ደግሞ ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች ለምሳሌ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች የሚሰጡትን አመራር በትሕትና መቀበልን ይጨምራል። እነዚህ ወንድሞች ልንታዘዛቸውና ልንገዛላቸው ከሚገቡ “አመራር የሚሰጡ” ወንድሞች መካከል ይገኙበታል። (ዕብ. 13:7, 17) አንዳንድ ውሳኔዎች የተደረጉበትን ምክንያት ሙሉ በሙሉ በማንረዳበት ጊዜም እንኳ ውሳኔዎቹን መደገፋችን ዘላቂ ጥቅም እንደሚያስገኝልን እናውቃለን። ይሖዋም ቃሉንና ድርጅቱን በመታዘዛችን ይባርከናል። በዚህ መንገድ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንደምንገዛ እናሳያለን።

15 በእርግጥም በታማኝና ልባም ባሪያ የምንተማመንበት በቂ ምክንያት አለን። የዚህ ሥርዓት አምላክ የሆነው ሰይጣን፣ የይሖዋንና የድርጅቱን ስም ለማጉደፍ የተቻለውን ሁሉ ጥረት እያደረገ ነው። (2 ቆሮ. 4:4) ለሰይጣን መሠሪ ዘዴዎች እጅ መስጠት የለብንም! (2 ቆሮ. 2:11) ወደ ጥልቁ ለመጣል “ጥቂት ጊዜ እንደቀረው” ስለሚያውቅ በተቻለው መጠን ብዙ የይሖዋ አገልጋዮች ከእሱ ጋር እንዲጠፉ ለማድረግ ቆርጦ ተነስቷል። (ራእይ 12:12) ይሁን እንጂ ሰይጣን ጥረቱን እያፋፋመ በሄደ መጠን እኛ ደግሞ ከምንጊዜውም ይበልጥ ወደ ይሖዋ እንቅረብ። ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ያሉትን ሕዝቦቹን ለመምራት እየተጠቀመበት ባለው መስመር ላይ ሙሉ በሙሉ እንተማመን። እንዲህ የምናደርግ ከሆነ አንድነት ያለው የወንድማማች ማኅበር ይኖረናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ