የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 3 ገጽ 14-ገጽ 15 አን. 3
  • አዳምና ሔዋን አምላክን ሳይታዘዙ ቀሩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዳምና ሔዋን አምላክን ሳይታዘዙ ቀሩ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መኖሪያቸውን ያጡት ለምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ከእኛ በላይ የሆኑ አሉ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • በገነት ውስጥ የነበረው ሕይወት ምን ይመስል ነበር?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • በችግር የተሞላ ኑሮ ተጀመረ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 3 ገጽ 14-ገጽ 15 አን. 3
አዳምና ሔዋን ከኤደን የአትክልት ስፍራ ሲወጡ

ትምህርት 3

አዳምና ሔዋን አምላክን ሳይታዘዙ ቀሩ

አዳም፣ ሔዋን የሰጠችውን ፍሬ ይዞ

አንድ ቀን ሔዋን ብቻዋን እያለች አንድ እባብ አነጋገራት። ‘አምላክ ከማንኛውም ዛፍ እንዳትበሉ ከልክሏችኋል?’ ብሎ ጠየቃት። ሔዋንም ‘ከአንዱ ዛፍ በስተቀር ከሌሎቹ ዛፎች ሁሉ መብላት እንችላለን። ከዚያ ዛፍ ፍሬ ከበላን ግን እንሞታለን’ አለችው። እባቡም ‘አትሞቱም። እንዲያውም ከዚያ ዛፍ ከበላችሁ እንደ አምላክ ትሆናላችሁ’ አላት። እባቡ የተናገረው ነገር እውነት ነበር? በፍጹም፣ ውሸት ነበር። ሔዋን ግን እባቡን አመነችው። ሔዋን ፍሬውን ትኩር ብላ ስትመለከተው የመብላት ፍላጎቷ እየጨመረ ሄደ። ከዚያም ፍሬውን ወስዳ በላች፤ ለአዳምም ሰጠችው። አዳም፣ አምላክን ካልታዘዙ እንደሚሞቱ ያውቅ የነበረ ቢሆንም ፍሬውን በላ።

አዳምና ሔዋን ከኤደን የአትክልት ስፍራ ከወጡ በኋላ መላእክትና የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ መግቢያውን ሲጠብቁ

ቀኑ እየመሸ ሲሄድ ይሖዋ አዳምንና ሔዋንን አነጋገራቸው። እሱን ሳይታዘዙ የቀሩት ለምን እንደሆነ ጠየቃቸው። ሔዋን በእባቡ አሳበበች፤ አዳም ደግሞ በሔዋን አሳበበ። አዳምና ሔዋን ስላልታዘዙ ይሖዋ ከአትክልት ስፍራው አስወጣቸው። ተመልሰው መግባት እንዳይችሉ በአትክልት ስፍራው መግቢያ ላይ መላእክትንና የሚሽከረከር የነበልባል ሰይፍ አስቀመጠ።

ሔዋንን ያነጋገራት እባቡ ራሱ አልነበረም። ይሖዋ እባብን መናገር እንዲችል አድርጎ አልፈጠረውም። እባቡን እንዲናገር ያደረገው አንድ ክፉ መልአክ ነው። ይሖዋ ለሔዋን ውሸት የነገራትን ይህን መልአክም እንደሚቀጣው ተናግሯል። ይህ ክፉ መልአክ ሰይጣን ዲያብሎስ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን እንዲህ ያደረገው ሔዋንን ለማታለል ብሎ ነው። ወደፊት ሰይጣን ሰዎችን ማታለሉን እንዳይቀጥል ይሖዋ ያጠፋዋል።

“ዲያብሎስ . . . ከመጀመሪያው አንስቶ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በእሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት ውስጥ ጸንቶ አልቆመም።”—ዮሐንስ 8:44 የግርጌ ማስታወሻ

ጥያቄ፦ ሔዋን ፍሬውን የበላችው ለምንድን ነው? አዳምና ሔዋን ይሖዋን ሳይታዘዙ በመቅረታቸው ምን ሆኑ? ሰይጣን ዲያብሎስ ማን ነው?

ዘፍጥረት 3:1-24፤ ዮሐንስ 8:44፤ 1 ዮሐንስ 3:8፤ ራእይ 12:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ