የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 33 ገጽ 82-ገጽ 83 አን. 2
  • ሩትና ናኦሚ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሩትና ናኦሚ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሩትና ናዖሚ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • “ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • የሩት መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • “ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 33 ገጽ 82-ገጽ 83 አን. 2
ናኦሚ ሩትን ወደ ቤቷ እንድትመለስ ስትነግራት

ትምህርት 33

ሩትና ናኦሚ

በአንድ ወቅት እስራኤል ውስጥ ረሃብ ተከስቶ ስለነበር ናኦሚ የተባለች አንዲት እስራኤላዊት ከባሏና ከሁለት ወንዶች ልጆቿ ጋር ወደ ሞዓብ ምድር ሄደች። ከጊዜ በኋላ የናኦሚ ባል ሞተ። ከዚያም ወንዶች ልጆቿ፣ ሩትና ዖርፋ የተባሉ ሞዓባውያን ሴቶችን አገቡ። የሚያሳዝነው ነገር የናኦሚ ወንዶች ልጆችም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሞቱ።

ናኦሚ የረሃቡ ወቅት እንዳበቃ ስትሰማ ወደ እስራኤል ለመመለስ ወሰነች። ሩትና ዖርፋም አብረዋት ለመሄድ ተነሱ፤ ነገር ግን መንገድ ላይ ሳሉ ናኦሚ እንዲህ አለቻቸው፦ ‘ለልጆቼ ጥሩ ሚስቶች፣ ለእኔ ደግሞ ጥሩ ምራቶች ነበራችሁ። ሁለታችሁም ሌላ ባል ብታገቡ ደስ ይለኛል። ወደ ቤታችሁ ተመለሱ።’ ሴቶቹም ‘እኛ በጣም እንወድሻለን! ትተንሽ መሄድ አንፈልግም’ አሏት። ናኦሚ ግን በድጋሚ እንዲመለሱ ነገረቻቸው። በመጨረሻም ዖርፋ ተመለሰች፤ ሩት ግን ለመመለስ ፈቃደኛ አልሆነችም። በዚህ ጊዜ ናኦሚ ሩትን እንዲህ አለቻት፦ ‘ዖርፋ ወደ ሕዝቧና ወደ አማልክቷ ተመልሳለች። አንቺም አብረሻት ተመለሺ፤ ወደ እናትሽ ቤት ሂጂ።’ ሩት ግን ‘ትቼሽ አልሄድም። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል’ አለቻት። ሩት እንዲህ ብላ ስትናገር ናኦሚ ምን የተሰማት ይመስልሃል?

ሩትና ናኦሚ እስራኤል የደረሱት ገብስ በሚታጨድበት ጊዜ ነበር። አንድ ቀን ሩት የተራረፈ እህል ለመሰብሰብ ቦዔዝ ወደተባለ ሰው እርሻ ሄደች፤ ቦዔዝ የረዓብ ልጅ ነበር። ቦዔዝ፣ ሩት በታማኝነት ናኦሚን ስትረዳ የቆየች ሞዓባዊት እንደሆነች ሰማ። ስለሆነም በእርሻ ቦታው ላይ የተወሰነ እህል ለሩት እንዲተዉላት ሠራተኞቹን ነገራቸው።

ሩት በቦዔዝ እርሻ ውስጥ እህል ስትሰበስብ

ማታ ላይ ናኦሚ ሩትን ‘ዛሬ ስትሠሪ የዋልሽው በማን እርሻ ውስጥ ነው?’ ብላ ጠየቀቻት። ሩትም ‘ቦዔዝ በተባለ ሰው እርሻ ውስጥ ነው’ አለቻት። ናኦሚም እንዲህ አለች፦ ‘ቦዔዝ እኮ የባሌ ዘመድ ነው። ከሌሎቹ ወጣት ሴቶች ጋር ሆነሽ በእሱ እርሻ ውስጥ መሥራትሽን ቀጥይ። በዚያ ምንም ችግር አይገጥምሽም።’

ናኦሚ ከቦዔዝ፣ ከሩትና ከኢዮቤድ ጋር

ሩት እህል የሚሰበሰብበት ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ በቦዔዝ እርሻ ውስጥ መሥራቷን ቀጠለች። ቦዔዝ፣ ሩት ጎበዝ ሠራተኛና ጥሩ ሴት እንደሆነች አስተዋለ። በዚያ ዘመን አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሞተ ዘመዱ የሆነ ሰው የሟቹን ሚስት እንዲያገባ ይደረግ ነበር። ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን አገባት። ከዚያም ኢዮቤድ የተባለ ልጅ ወለዱ፤ ኢዮቤድ ከጊዜ በኋላ የንጉሥ ዳዊት አያት ሆኗል። የናኦሚ ጓደኞች በጣም ተደሰቱ። በመሆኑም ናኦሚን እንዲህ አሏት፦ ‘ይሖዋ በመጀመሪያ ጥሩ ረዳት እንድትሆንሽ ሩትን ሰጠሽ፤ አሁን ደግሞ የልጅ ልጅ አገኘሽ። ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን።’

“ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።”—ምሳሌ 18:24

ጥያቄ፦ ሩት ለናኦሚ ያላትን ፍቅር ያሳየችው እንዴት ነው? ይሖዋ ሩትንና ናኦሚን የተንከባከባቸው እንዴት ነው?

ሩት 1:1–4:22፤ ማቴዎስ 1:5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ