የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 48 ገጽ 116-ገጽ 117 አን. 1
  • የአንዲት ድሃ ሴት ልጅ ከሞት ተነሳ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንዲት ድሃ ሴት ልጅ ከሞት ተነሳ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሰራፕታ የነበረችው መበለት ያሳየችው እምነት ክሷታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የኤልያስን የመሰለ እምነት አለህን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • አምላኩ አጽናንቶታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 48 ገጽ 116-ገጽ 117 አን. 1
ኤልያስ እንጨት የምትለቅመውን ሴት ሲያናግራት

ትምህርት 48

የአንዲት ድሃ ሴት ልጅ ከሞት ተነሳ

የዱቄት ማድጋና የዘይት ማሰሮ

በድርቁ ወቅት ይሖዋ ኤልያስን እንዲህ አለው፦ ‘ወደ ሰራፕታ ሂድ። በዚያ የምትኖር አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት ምግብ ትሰጥሃለች።’ ኤልያስ ወደ ከተማዋ መግቢያ እንደደረሰ ይሖዋ በነገረው መሠረት አንዲት ድሃ ሴት እንጨት ስትለቅም አየ። ከዚያም የሚጠጣው ውኃ እንድትሰጠው ጠየቃት። ውኃ ለማምጣት ስትሄድ ድጋሚ ጠራትና ‘እባክሽ ቁራሽ ዳቦም ይዘሽልኝ ነይ’ አላት። ሴትየዋ ግን ‘የምሰጥህ ዳቦ የለኝም። እንዳልጋግርልህ እንኳ ያለኝ ዱቄትና ዘይት ለእኔና ለልጄ ትንሽ ዳቦ ለመጋገር ብቻ የሚበቃ ነው’ አለችው። ኤልያስም ‘ለእኔ ዳቦ ከጋገርሽልኝ ዳግመኛ ዝናብ እስኪዘንብ ድረስ ዱቄቱና ዘይቱ እንደማያልቅ ይሖዋ ተናግሯል’ አላት።

ስለዚህ ሴትየዋ ወደ ቤት ገብታ ለይሖዋ ነቢይ ዳቦ ጋገረችለት። ልክ ይሖዋ ቃል እንደገባው በድርቁ ወቅት ሴትየዋና ልጇ የሚበሉት ምግብ አላጡም። ዱቄቱም ሆነ ዘይቱ አላለቀም።

ከዚያም አንድ በጣም የሚያሳዝን ነገር ተፈጠረ። የሴትየዋ ልጅ በጣም ታመመና ሞተ። እሷም ኤልያስን እንዲረዳት ለመነችው። ኤልያስም ትንሹን ልጅ ከእሷ ተቀብሎ በሰገነቱ ላይ ወዳለ ክፍል ወሰደው። ከዚያም አልጋ ላይ አስተኛውና ‘ይሖዋ፣ እባክህ ይህን ልጅ አስነሳው’ በማለት ጸለየ። ይሖዋ ልጁን ከሞት ቢያስነሳው በጣም አስደናቂ ተአምር ይሆናል። ምክንያቱም እስከምናውቀው ድረስ ከዚያ በፊት ማንም ሰው ከሞት ተነስቶ አያውቅም። በተጨማሪም ይህች ሴትና ልጇ እስራኤላውያን አልነበሩም።

ሆኖም የልጁ ሕይወት ተመለሰለትና መተንፈስ ጀመረ! ኤልያስም ሴትየዋን ‘ይኸው! ልጅሽ ተነስቷል’ አላት። እሷም በጣም ተደስታ ኤልያስን እንዲህ አለችው፦ ‘አንተ በእርግጥም የአምላክ ሰው ነህ። ምክንያቱም የምትናገረው ይሖዋ እንድትናገር ያዘዘህን ነገር ብቻ ነው፤ የተናገርከውም ነገር ሁልጊዜ ይፈጸማል።’

ኤልያስ ከሞት የተነሳውን ልጅ ለእናቱ ሲሰጣት

“ቁራዎችን ተመልከቱ፦ አይዘሩም፣ አያጭዱም እንዲሁም የእህል ማከማቻ ወይም ጎተራ የላቸውም፤ ሆኖም አምላክ ይመግባቸዋል። ታዲያ እናንተ ከወፎች እጅግ የላቀ ዋጋ የላችሁም?”—ሉቃስ 12:24

ጥያቄ፦ በሰራፕታ የምትኖረው ሴት በይሖዋ እንደምትታመን ያሳየችው እንዴት ነው? ኤልያስ እውነተኛ የአምላክ ነቢይ እንደሆነ እንዴት እናውቃለን?

1 ነገሥት 17:8-24፤ ሉቃስ 4:25, 26

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ