የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 55 ገጽ 132
  • የይሖዋ መልአክ ሕዝቅያስን አዳነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ መልአክ ሕዝቅያስን አዳነው
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ንጉሡ ያሳየው እምነት ተካሰ
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
  • አምላክ ንጉሥ ሕዝቅያስን ረዳው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • በዛሬው ጊዜ ሰባቱ እረኞችና ስምንቱ አለቆች እነማን ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ከዚህ ዓለም የሚገኝ እርዳታ የለም
    የኢሳይያስ ትንቢት—ለመላው የሰው ዘር የፈነጠቀ ብርሃን ጥራዝ 1
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 55 ገጽ 132
አንድ መልአክ የአሦራውያንን ወታደሮች ሲገድል

ትምህርት 55

የይሖዋ መልአክ ሕዝቅያስን አዳነው

የአሦር መንግሥት ከአሥሩ ነገድ የእስራኤል መንግሥት ጋር ተዋግቶ በማሸነፍ እስራኤላውያንን መግዛት ጀመረ። አሁን ደግሞ የአሦር ንጉሥ የሆነው ሰናክሬም የሁለቱን ነገድ የይሁዳ መንግሥት በማሸነፍ አይሁዳውያንንም መግዛት ፈለገ። በመሆኑም የይሁዳን ከተሞች አንድ በአንድ መውሰድ ጀመረ። ሆኖም በዋነኝነት መያዝ የፈለገው ኢየሩሳሌምን ነው። ሰናክሬም ይሖዋ ኢየሩሳሌምን እንደሚጠብቃት አላወቀም ነበር።

የይሁዳ ንጉሥ የሆነው ሕዝቅያስ፣ ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን እንዳይወጋ ለማድረግ ሲል ብዙ ገንዘብ ሰጠው። ሰናክሬም ግን ገንዘቡን የወሰደ ቢሆንም እንኳ ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ ኃይለኛ የሆኑትን ወታደሮቹን ላከ። አሦራውያኑ ወደ ኢየሩሳሌም እየተጠጉ ሲመጡ የከተማዋ ነዋሪዎች በጣም ፈሩ። በዚህ ጊዜ ሕዝቅያስ እንዲህ አላቸው፦ ‘አትፍሩ። አሦራውያን ኃይለኛ ተዋጊዎች ቢሆኑም እንኳ ይሖዋ እኛን ከእነሱ የበለጠ ኃይለኛ ሊያደርገን ይችላል።’

ሰናክሬም መልእክተኛውን ራብሻቁን ወደ ኢየሩሳሌም በመላክ በሕዝቡ ላይ እንዲያሾፍባቸው አደረገ። ራብሻቁ ከከተማዋ ውጭ ቆሞ እንዲህ በማለት ጮክ ብሎ ተናገረ፦ ‘ይሖዋ ሊረዳችሁ አይችልም። ሕዝቅያስ አያታላችሁ። እናንተን ከእኛ ሊያድናችሁ የሚችል አምላክ የለም።’

ሕዝቅያስ ምን ማድረግ እንዳለበት ይሖዋን ጠየቀ። ይሖዋም እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ ‘ራብሻቁ የተናገረው ነገር ሊያስፈራህ አይገባም። ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን መያዝ አይችልም።’ ከዚያም ሰናክሬም ለሕዝቅያስ ደብዳቤ ላከለት። ደብዳቤው እንዲህ የሚል ነበር፦ ‘እጅ ብትሰጥ ይሻልሃል። ይሖዋ ሊያድንህ አይችልም።’ ሕዝቅያስ እንዲህ በማለት ጸለየ፦ ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሰዎች ሁሉ አንተ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ መሆንህን እንዲያውቁ ስትል እባክህ አድነን።’ ይሖዋም እንዲህ አለው፦ ‘የአሦር ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም አይገባም። ኢየሩሳሌምን እኔ ራሴ አድናታለሁ።’

ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን እንደሚይዛት እርግጠኛ ሆኖ ነበር። ሆኖም ሌሊት ላይ ይሖዋ የአሦር ወታደሮች ወደሰፈሩበት ከከተማዋ ውጭ ወደሚገኝ ቦታ መልአኩን ላከ። መልአኩ 185,000 ወታደሮችን ገደለ! ንጉሥ ሰናክሬም ኃይለኛ የሆኑት ወታደሮቹ ተገደሉበት። ስለዚህ በደረሰበት ሽንፈት አፍሮ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት ሕዝቅያስንና ኢየሩሳሌምን አዳነ። አንተ በዚያ ወቅት ኢየሩሳሌም ውስጥ ብትኖር ኖሮ በይሖዋ ትታመን ነበር?

“የይሖዋ መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል።”—መዝሙር 34:7

ጥያቄ፦ ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ያዳናት እንዴት ነው? ይሖዋ አንተንም ሊያድንህ እንደሚችል ትተማመናለህ?

2 ነገሥት 17:1-6፤ 18:13-37፤ 19:1-37፤ 2 ዜና መዋዕል 32:1-23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ