የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 56 ገጽ 134
  • ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢዮስያስ ጥሩ ጓደኞች ነበሩት
    ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ትሑት የነበረው ኢዮስያስ የይሖዋን ሞገስ አግኝቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • የመጨረሻው የእስራኤል ጥሩ ንጉሥ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢዮስያስ ትክክል የሆነውን ለማድረግ መርጧል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 56 ገጽ 134
ሳፋን የሕጉን መጽሐፍ ለንጉሥ ኢዮስያስ ሲያነብለት

ትምህርት 56

ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር

ኢዮስያስ የስምንት ዓመት ልጅ ሳለ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ። በዚያ ዘመን ሕዝቡ የአስማት ድርጊቶች ይፈጽምና ጣዖት ያመልክ ነበር። ኢዮስያስ 16 ዓመት ሲሆነው ይሖዋን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ጥረት ማድረግ ጀመረ። በ20 ዓመቱ ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙትን ጣዖታትና መሠዊያዎች ማጥፋት ጀመረ። ኢዮስያስ 26 ዓመት ሲሆነው የይሖዋ ቤተ መቅደስ እንዲታደስ አደረገ።

ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የይሖዋን ሕግ መጽሐፍ አገኘ፤ ምናልባትም ይህ መጽሐፍ ሙሴ ራሱ የጻፈው ሊሆን ይችላል። የንጉሡ ጸሐፊ የሆነው ሳፋን መጽሐፉን ወደ ኢዮስያስ አምጥቶ ሕጉን ጮክ ብሎ አነበበለት። ኢዮስያስም የሕጉን ቃል ሲሰማ ሕዝቡ ለብዙ ዓመታት ይሖዋን እንዳልታዘዙ ተገነዘበ። ንጉሥ ኢዮስያስ ኬልቅያስን እንዲህ አለው፦ ‘ይሖዋን በጣም አስቆጥተነዋል። ሂድና ይሖዋን ጠይቅ። ምን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል።’ ይሖዋም በነቢዪቱ ሕልዳና አማካኝነት እንዲህ በማለት መልስ ሰጠ፦ ‘የይሁዳ ሰዎች ትተውኛል። ስለዚህ መቀጣት አለባቸው፤ የሚቀጡት ግን ኢዮስያስ ንጉሥ ሆኖ በሚገዛበት ዘመን አይደለም፤ ምክንያቱም እሱ ራሱን ዝቅ አድርጓል።’

ኬልቅያስ የይሖዋን ሕግ የያዘውን መጽሐፍ ሲያገኝ

ንጉሥ ኢዮስያስ መልእክቱን ሲሰማ ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደና የይሁዳን ሕዝብ ሰበሰበ። ከዚያም የይሖዋን ሕግ ለመላው ሕዝብ ጮክ ብሎ አነበበ። ኢዮስያስና ሕዝቡም፣ በሙሉ ልባቸው ይሖዋን ለመታዘዝ ቃል ገቡ።

የይሁዳ ሰዎች የፋሲካን በዓል ካከበሩ ብዙ ዓመታት አልፈው ነበር። ሆኖም ኢዮስያስ የፋሲካ በዓል በየዓመቱ መከበር እንዳለበት በሕጉ መጽሐፍ ላይ ሲያነብ ሕዝቡን ‘ለይሖዋ ፋሲካ እናደርጋለን’ አላቸው። ከዚያም ኢዮስያስ ብዙ መሥዋዕት አዘጋጀ፤ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚዘምሩ ዘማሪዎችን መደበ። ከዚያም የይሁዳ ሰዎች ፋሲካን አከበሩ፤ ቀጥሎም ለሰባት ቀን ያህል የቂጣ በዓልን አከበሩ። ከሳሙኤል ዘመን አንስቶ እንደዚህ ያለ የፋሲካ በዓል ተከብሮ አያውቅም ነበር። ኢዮስያስ በእርግጥም የአምላክን ሕግ ይወድ ነበር። አንተስ ስለ ይሖዋ መማር ያስደስትሃል?

“ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።”—መዝሙር 119:105

ጥያቄ፦ ንጉሥ ኢዮስያስ የአምላክን ሕግ ሲሰማ ምን አደረገ? ይሖዋ ለኢዮስያስ ምን አመለካከት ነበረው?

2 ነገሥት 21:26፤ 22:1–23:30፤ 2 ዜና መዋዕል 34:1–35:25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ