የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 69 ገጽ 164-ገጽ 165 አን. 2
  • ገብርኤል ማርያምን አነጋገራት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ገብርኤል ማርያምን አነጋገራት
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንድ መልአክ ማርያምን አነጋገራት
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ከመወለዱ በፊት ክብር ተሰጥቶታል
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኢየሱስ ከመወለዱ በፊት ክብር ተሰጥቶታል
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • “እነሆ፣ እኔ የይሖዋ ባሪያ ነኝ!”
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 69 ገጽ 164-ገጽ 165 አን. 2
መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ሲያናግራት

ትምህርት 69

ገብርኤል ማርያምን አነጋገራት

አንድ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ሲገለጥለት

ኤልሳቤጥ ማርያም የምትባል አንዲት ወጣት ዘመድ ነበረቻት፤ ማርያም የምትኖረው በገሊላ በምትገኘው በናዝሬት ከተማ ነበር። ማርያም የአናጺነት ሙያ የነበረው ዮሴፍ የተባለ እጮኛ ነበራት። ኤልሳቤጥ የስድስት ወር እርጉዝ በነበረችበት ወቅት መልአኩ ገብርኤል ማርያምን አነጋገራት። እንዲህ አላት፦ ‘ማርያም፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን። ይሖዋ እጅግ ባርኮሻል።’ ማርያም፣ ገብርኤል ምን ማለቱ እንደሆነ አልገባትም። ከዚያም እንዲህ አላት፦ ‘ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ፤ ስሙን ኢየሱስ ትይዋለሽ። እሱም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል። መንግሥቱም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።’

ማርያምም ‘እኔ እኮ ከወንድ ጋር ተኝቼ አላውቅም። ታዲያ እንዴት ልጅ ልወልድ እችላለሁ?’ አለችው። ገብርኤልም እንዲህ አላት፦ ‘ይሖዋ የሚያቅተው ነገር የለም። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ ከዚያም ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ። ዘመድሽ ኤልሳቤጥም አርግዛለች።’ ማርያምም ‘እኔ የይሖዋ ባሪያ ነኝ። ልክ እንደተናገርከው ይሁንልኝ’ አለች።

ዮሴፍ እርጉዟን ማርያምን ሚስቱ አድርጎ ሲወስዳት

ማርያም ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ በተራራ ላይ ወደምትገኝ አንዲት ከተማ ሄደች። ኤልሳቤጥ የማርያምን ሰላምታ ስትሰማ በሆዷ ውስጥ ያለው ልጅ ዘለለ። በዚህ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ እንዲህ አለች፦ ‘ማርያም፣ ይሖዋ ባርኮሻል። የመሲሑ እናት ወደ ቤቴ መምጣቷ ለእኔ ትልቅ ክብር ነው።’ ማርያምም ‘በሙሉ ልቤ ይሖዋን አወድሰዋለሁ’ አለች። ማርያም ለሦስት ወር ያህል ከኤልሳቤጥ ጋር ቆየች፤ ከዚያም በናዝሬት ወደሚገኘው ቤቷ ተመለሰች።

ዮሴፍ፣ ማርያም ማርገዟን ሲያውቅ ከሌላ ወንድ ያረገዘች ስለመሰለው ሊተዋት አሰበ። ሆኖም አንድ መልአክ በሕልም ተገልጦለት ‘ማርያምን ለማግባት አትፍራ። ምንም የሠራችው ጥፋት የለም’ አለው። ስለዚህ ዮሴፍ ማርያምን አገባት፤ ወደ ቤቱም ወሰዳት።

“በሰማይና በምድር . . . ይሖዋ ደስ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።”—መዝሙር 135:6

ጥያቄ፦ ገብርኤል ለማርያም የምትወልደውን ልጅ በተመለከተ ምን ነገራት? ኤልሳቤጥና ማርያም የገጠማቸውን ሁኔታ በተመለከተ ምን ተሰማቸው?

ማቴዎስ 1:18-25፤ ሉቃስ 1:26-56፤ ኢሳይያስ 7:14፤ 9:7፤ ዳንኤል 2:44፤ ገላትያ 4:4

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ