የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 70 ገጽ 166-ገጽ 167 አን. 2
  • መላእክት ኢየሱስ መወለዱን ተናገሩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መላእክት ኢየሱስ መወለዱን ተናገሩ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ ጋጣ ውስጥ ተወለደ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢየሱስ ተወለደ—የትና መቼ?
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ኢየሱስ ክርስቶስ—በአእምሯችን ልናስበው የሚገባው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 70 ገጽ 166-ገጽ 167 አን. 2
መላእክት ኢየሱስ መወለዱን ለእረኞቹ ሲናገሩ

ትምህርት 70

መላእክት ኢየሱስ መወለዱን ተናገሩ

የሮም ንጉሠ ነገሥት የነበረው አውግስጦስ ቄሳር ሁሉም አይሁዳውያን ወደተወለዱበት ከተማ ሄደው እንዲመዘገቡ አዘዘ። ስለዚህ ዮሴፍና ማርያም የዮሴፍ ቤተሰቦች ይኖሩባት ወደነበረችው ወደ ቤተልሔም ሄዱ። በዚህ ጊዜ ማርያም ልትወልድ ተቃርባ ነበር።

ቤተልሔም ሲደርሱ ያገኙት የማረፊያ ቦታ የከብቶች በረት ብቻ ነበር። በዚያም ማርያም ኢየሱስን ወለደች። ከዚያም በጨርቅ ጠቅልላ ግርግም ውስጥ አስተኛችው።

በቤተልሔም አቅራቢያ ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ የሚያድሩ እረኞች ነበሩ። በድንገት አንድ መልአክ በፊታቸው ቆመ፤ የይሖዋም ክብር በዙሪያቸው አንጸባረቀ። በዚህ ጊዜ እረኞቹ በጣም ፈሩ፤ መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ ‘አትፍሩ። አንድ ደስ የሚል ዜና እነግራችኋለሁ። መሲሑ ዛሬ በቤተልሔም ተወልዷል።’ ወዲያውኑም በሰማይ ላይ ብዙ መላእክት ታይተው ‘በሰማይ ለአምላክ ክብር ይሁን፤ በምድርም ላይ ሰላም ይሁን’ አሉ። ከዚያም መላእክቱ ተሰወሩ። በዚህ ጊዜ እረኞቹ ምን አደረጉ?

እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‘አሁኑኑ ወደ ቤተልሔም እንሂድ’ ተባባሉ። ከዚያም በፍጥነት ወደ ቤተልሔም ሄዱ፤ ዮሴፍንና ማርያምንም ከአዲሱ ልጃቸው ጋር በረት ውስጥ አገኟቸው።

መልአኩ ለእረኞቹ የተናገረውን ነገር የሰሙ ሰዎች በሙሉ በጣም ተደነቁ። ማርያም መልአኩ የተናገረውን ነገር በደንብ አሰበችበት፤ ከዚያ በኋላም ጨርሶ አልረሳችውም። እረኞቹ ስላዩትና ስለሰሙት ነገር ይሖዋን እያመሰገኑ ወደ መንጎቻቸው ተመለሱ።

“እኔ ወደዚህ የመጣሁት ከእሱ ዘንድ [ነው]። እሱ ላከኝ እንጂ እኔ በራሴ ተነሳስቼ አልመጣሁም።”—ዮሐንስ 8:42

ጥያቄ፦ መላእክት ኢየሱስ መወለዱን የተናገሩት እንዴት ነው? እረኞቹ ወደ ቤተልሔም ሲሄዱ ማንን አገኙ?

ሉቃስ 2:1-20፤ ኢሳይያስ 9:6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ