የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 74 ገጽ 176-ገጽ 177 አን. 4
  • ኢየሱስ መሲሕ ሆነ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ መሲሕ ሆነ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዮሐንስ ኢየሱስን አጠመቀው
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢየሱስ ተጠመቀ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የመሲሑ መንገድ ጠራጊ ነበር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጀ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 74 ገጽ 176-ገጽ 177 አን. 4
ዮሐንስ ኢየሱስን ካጠመቀው በኋላ የአምላክ መንፈስ በኢየሱስ ላይ እንደ ርግብ ወረደ

ትምህርት 74

ኢየሱስ መሲሕ ሆነ

መጥምቁ ዮሐንስ ‘ከእኔ የሚበልጥ ይመጣል’ እያለ ይሰብክ ነበር። ኢየሱስ 30 ዓመት ሲሆነው ከገሊላ ተነስቶ ዮሐንስ ወደሚያጠምቅበት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ። ኢየሱስ፣ ዮሐንስ እንዲያጠምቀው ፈልጎ ነበር፤ ዮሐንስ ግን ‘እኔ አንተን ማጥመቅ የለብኝም። እንዲያውም እኔን ማጥመቅ ያለብህ አንተ ነህ’ አለው። ኢየሱስ ግን ዮሐንስን ‘ይሖዋ፣ አንተ እንድታጠምቀኝ ይፈልጋል’ አለው። ስለዚህ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ገቡ፤ ዮሐንስም ኢየሱስን ሙሉ በሙሉ ውኃው ውስጥ በማጥለቅ አጠመቀው።

ኢየሱስ ከውኃው ከወጣ በኋላ ጸለየ። ወዲያውኑም ሰማያት ተከፈቱ፤ የአምላክም መንፈስ በእሱ ላይ እንደ ርግብ ወረደ። ከዚያም ይሖዋ ከሰማይ እንዲህ በማለት ተናገረ፦ “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል።”

ኢየሱስ የይሖዋ መንፈስ ሲወርድበት መሲሕ ወይም ክርስቶስ ሆነ። ከዚያም ይሖዋ በምድር ላይ እንዲያከናውነው የሰጠውን ሥራ መሥራት ጀመረ።

ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወደ ምድረ በዳ ሄዶ በዚያ 40 ቀን ቆየ። ከምድረ በዳ ሲመለስ ወደ ዮሐንስ ሄደ። ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ወደ እሱ ሲመጣ አይቶ ‘የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደው የአምላክ በግ ይህ ነው’ አለ። ዮሐንስ ይህን ሲል ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን ለሕዝቡ ማሳወቁ ነበር። ኢየሱስ በምድረ በዳ በነበረበት ወቅት ምን እንዳጋጠመው ታውቃለህ? እስቲ እንመልከት።

“‘አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል’ የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።”—ማርቆስ 1:11

ጥያቄ፦ ኢየሱስ የተጠመቀው ለምንድን ነው? ዮሐንስ ኢየሱስን ‘የአምላክ በግ’ በማለት የጠራው ለምንድን ነው?

ማቴዎስ 3:13-17፤ ማርቆስ 1:9-11፤ ሉቃስ 3:21-23፤ ዮሐንስ 1:29-34፤ ኢሳይያስ 42:1፤ ዕብራውያን 10:7-9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ