የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 76 ገጽ 180-ገጽ 181 አን. 2
  • ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ቤተ መቅደሱን አጸዳ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ለእውነተኛው አምልኮ ቅንዓት አሳየ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ለይሖዋ አምልኮ ያሳየው ቅንዓት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ቤተ መቅደሱ እንደገና ጸዳ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 76 ገጽ 180-ገጽ 181 አን. 2
ኢየሱስ እንስሳቱን በጅራፍ ከቤተ መቅደሱ አስወጣ፤ እንዲሁም የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛ ገለባበጠ

ትምህርት 76

ኢየሱስ ነጋዴዎችን ከቤተ መቅደሱ አባረረ

በ30 ዓ.ም. በሚያዝያ ወር አካባቢ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ። ብዙ ሰዎች ፋሲካን ለማክበር ወደ ከተማዋ መጥተው ነበር። በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ሰዎች በቤተ መቅደሱ ውስጥ የእንስሳት መሥዋዕት ያቀርቡ ነበር። አንዳንድ ሰዎች ከሚኖሩበት ቦታ እንስሳት ይዘው ይመጡ ነበር፤ ሌሎቹ ደግሞ እንስሳቱን ከኢየሩሳሌም ይገዙ ነበር።

ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደሱ ሲገባ በዚያ እንስሳት የሚሸጡ ሰዎችን አየ። ይሖዋ በሚመለክበት ቤት ውስጥ ንግድ ጀምረው ነበር። ታዲያ ኢየሱስ ይህን ሲያይ ምን አደረገ? በገመድ ጅራፍ ሠርቶ በጎቹንና ከብቶቹን ከቤተ መቅደሱ አስወጣ። ከዚያም የገንዘብ መንዛሪዎቹን ጠረጴዛ በመገለባበጥ ሳንቲሞቻቸውን መሬት ላይ በተነ። ርግብ የሚሸጡትንም ሰዎች ‘እነዚህን ከዚህ አውጡ! የአባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት!’ አላቸው።

በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ኢየሱስ ባደረገው ነገር ተገረሙ። ደቀ መዛሙርቱም ስለ መሲሑ የተነገረውን ‘ለይሖዋ ቤት ከፍተኛ ቅንዓት አለኝ’ የሚለውን ትንቢት አስታወሱ።

ከጊዜ በኋላም በ33 ዓ.ም. ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚነግዱትን ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ አባሯል። ለአባቱ ቤት ንቀት በሚያሳዩ ሰዎች ላይ እርምጃ ወስዷል።

“ለአምላክም ለሀብትም በአንድ ጊዜ ባሪያ መሆን አትችሉም።”—ሉቃስ 16:13

ጥያቄ፦ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንስሳት የሚሸጡትን ሰዎች ሲያይ ምን አደረገ? ኢየሱስ እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?

ማቴዎስ 21:12, 13፤ ማርቆስ 11:15-17፤ ሉቃስ 19:45, 46፤ ዮሐንስ 2:13-17፤ መዝሙር 69:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ