የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 77 ገጽ 182-ገጽ 183 አን. 2
  • ውኃ ልትቀዳ የመጣችው ሳምራዊት ሴት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ውኃ ልትቀዳ የመጣችው ሳምራዊት ሴት
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዲት ሳምራዊት አስተማረ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • አንዲት ሳምራዊት ሴት አስተማረ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ከአንዲት ሴት ጋር በውኃው ጉድጓድ አጠገብ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ሕይወት የሚያስገኝ ውኃ
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 77 ገጽ 182-ገጽ 183 አን. 2
ኢየሱስ በያዕቆብ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ አንዲትን ሳምራዊት ሴት ሲያነጋግር

ትምህርት 77

ውኃ ልትቀዳ የመጣችው ሳምራዊት ሴት

ፋሲካ ከተከበረ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ ሲመለሱ በሰማርያ በኩል አለፉ። ሰማርያ ውስጥ ሲካር የተባለች ከተማ አቅራቢያ ሲደርሱ ኢየሱስ የያዕቆብ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ አረፍ አለ። በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ሊገዙ ወደ ከተማዋ ሄዱ።

ከዚያም አንዲት ሴት ውኃ ለመቅዳት ወደ ጉድጓዱ መጣች። ኢየሱስም “እባክሽ፣ የምጠጣው ውኃ ስጪኝ” አላት። እሷም እንዲህ አለችው፦ ‘ለምንድን ነው የምታነጋግረኝ? እኔ ሳምራዊት ሴት ነኝ። አይሁዳውያን ደግሞ ከሳምራውያን ጋር አይነጋገሩም።’ ኢየሱስ ግን እንዲህ አላት፦ ‘እኔ ማን እንደሆንኩ ብታውቂ ኖሮ አንቺ ራስሽ ውኃ እንድሰጥሽ ትጠይቂኝ ነበር፤ እኔም ሕይወት የሚያስገኝ ውኃ እሰጥሽ ነበር።’ ሴትየዋም ‘ምን ማለትህ ነው? አንተ የውኃ መቅጃ እንኳ የለህም’ አለችው። ከዚያም ኢየሱስ ‘እኔ የምሰጠውን ውኃ የሚጠጣ ሰው ድጋሚ አይጠማም’ አላት። ሴትየዋም ‘ጌታዬ፣ እባክህ ይህን ውኃ ስጠኝ’ አለችው።

ከዚያም ኢየሱስ ‘ሂጂና ባልሽን ይዘሽ ነይ’ አላት። እሷም ‘ባል የለኝም’ አለችው። እሱም እንዲህ አላት፦ ‘እውነትሽን ነው። አምስት ጊዜ አግብተሽ ነበር፤ አሁን አብሮሽ የሚኖረው ሰው ደግሞ ባልሽ አይደለም።’ ሴትየዋም እንዲህ አለች፦ ‘ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደሆንክ አሁን አወቅኩ። እኛ ሳምራውያን በዚህ ተራራ ላይ አምላክን ማምለክ እንደምንችል እናምናለን፤ አይሁዳውያን ግን ማምለክ የምንችለው በኢየሩሳሌም ብቻ እንደሆነ ይናገራሉ። መሲሑ ሲመጣ አምላክን እንዴት ማምለክ እንዳለብን እንደሚነግረን አምናለሁ።’ ኢየሱስም ‘መሲሑ እኔ ነኝ’ በማለት ከዚያ በፊት ለማንም ሰው ተናግሮ የማያውቀውን ነገር ነገራት።

ኢየሱስ ሳምራውያንን ሲያነጋግር

ሴትየዋ በፍጥነት ወደ ከተማዋ ሄደችና ሳምራውያኑን እንዲህ አለቻቸው፦ ‘መሲሑን ያገኘሁት መሰለኝ። እሱ ስለ እኔ ሁሉንም ነገር ያውቃል። መጥታችሁ ማየት ትችላላችሁ!’ እነሱም እሷን ተከትለው ወደ ጉድጓዱ ሄዱና ኢየሱስ ሲያስተምር ያዳምጡ ጀመር።

ሳምራውያኑ ኢየሱስን በከተማቸው ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት እንዲቆይ ጠየቁት። ኢየሱስም ለሁለት ቀናት በዚያ የሚገኙ ሰዎችን አስተማረ፤ ብዙ ሰዎችም በእሱ አመኑ። እነሱም ሳምራዊቷን ሴት ‘አሁን ኢየሱስ የሚያስተምረውን እኛ ራሳችን ስለሰማን እሱ በእርግጥ የዓለም አዳኝ እንደሆነ አውቀናል’ አሏት።

“‘ና!’ . . . የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግ ሁሉ የሕይወትን ውኃ በነፃ ይውሰድ።”—ራእይ 22:17

ጥያቄ፦ ሳምራዊቷ ሴት ኢየሱስ ስላነጋገራት የተገረመችው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ለሳምራዊቷ ሴት ምን ነገራት?

ዮሐንስ 4:1-42

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ