የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 81 ገጽ 190-ገጽ 191 አን. 1
  • የተራራው ስብከት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የተራራው ስብከት
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ታላቅ አስተማሪ የነበረው ለምንድን ነው?
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • መልካም ማድረጋችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • “ወዳጆች ብዬ ጠርቻችኋለሁ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • ስለ አምላክ መማር ይኖርብሃል
    የአምላክ ወዳጅ መሆን ትችላለህ!
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 81 ገጽ 190-ገጽ 191 አን. 1
ብዙ ሰዎች ተሰብስበው የኢየሱስን የተራራ ስብከት ሲያዳምጡ

ትምህርት 81

የተራራው ስብከት

ኢየሱስ 12 ሐዋርያቱን ከመረጠ በኋላ ከተራራው ወርዶ ብዙ ሕዝብ ወደተሰበሰበበት ቦታ ሄደ። ሰዎቹ የመጡት ከገሊላ፣ ከይሁዳ፣ ከጢሮስ፣ ከሲዶና፣ ከሶርያና ከዮርዳኖስ ማዶ ሲሆን የታመሙና በአጋንንት የተያዙ ሰዎችን ይዘው መጥተው ነበር። ኢየሱስ ሁሉንም ፈወሳቸው። ከዚያም ተራራው ላይ ተቀምጦ መናገር ጀመረ። የይሖዋ ወዳጅ መሆን ከፈለግን ምን ማድረግ እንዳለብን ተናገረ። የይሖዋ አመራር እንደሚያስፈልገን ማወቅና እሱን መውደድ አለብን። ሆኖም ሌሎች ሰዎችን የማንወድ ከሆነ ‘አምላክን እወደዋለሁ’ ማለት አንችልም። ጠላቶቻችንን ጨምሮ ለሰው ሁሉ ደግና የማናዳላ መሆን አለብን።

ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ ‘ጓደኞቻችሁን ብቻ መውደዳችሁ በቂ አይደለም። ጠላቶቻችሁንም መውደድና ሰዎችን ከልባችሁ ይቅር ማለት አለባችሁ። አንድን ሰው ቅር ካሰኛችሁ ቶሎ ወደ እሱ ሄዳችሁ ይቅርታ ጠይቁ። ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው።’

ብዙ ሰዎች ተሰብስበው የኢየሱስን የተራራ ስብከት ሲያዳምጡ

በተጨማሪም ኢየሱስ ለሰዎቹ ገንዘብን በተመለከተ ጥሩ ምክር ሰጥቷቸዋል። እንዲህ አላቸው፦ ‘የይሖዋ ወዳጅ መሆን ሀብታም ከመሆን ይበልጥ አስፈላጊ ነው። ገንዘባችሁን ሌባ ሊሰርቀው ይችላል፤ ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ወዳጅነት ግን ማንም ሊሰርቅባችሁ አይችልም። ምን እንበላለን፣ ምን እንጠጣለን ወይም ምን እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ። ወፎችን ተመልከቱ። አምላክ ሁልጊዜ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ ይሰጣቸዋል። መጨነቃችሁ በዕድሜያችሁ ላይ አንድም ቀን ሊጨምርላችሁ አይችልም። ይሖዋ ምን እንደሚያስፈልጋችሁ ያውቃል።’

የተሰበሰቡት ሰዎች ማንም ሰው እንደ ኢየሱስ ሲያስተምር ሰምተው አያውቁም ነበር። የሃይማኖት መሪዎቻቸው የሆኑት ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን እነዚህን ነገሮች አላስተማሯቸውም። ኢየሱስ እንዲህ ያለ ጥሩ አስተማሪ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? የሚያስተምረው ከይሖዋ የተማረውን ብቻ ስለነበረ ነው።

“ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ ገርና በልቤ ትሑት ነኝ፤ ለራሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ።”—ማቴዎስ 11:29

ጥያቄ፦ የይሖዋ ወዳጅ መሆን ከፈለግን ምን ማድረግ አለብን? ይሖዋ ለሌሎች ሰዎች ምን ዓይነት ባሕርይ እንድታሳይ ይፈልጋል?

ማቴዎስ 4:24–5:48፤ 6:19-34፤ 7:28, 29፤ ሉቃስ 6:17-31

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ