የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 83 ገጽ 194-ገጽ 195 አን. 1
  • ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጥቂት ዳቦና ዓሣ ሺዎችን መመገብ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን በተአምር መገበ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ከዳቦው ተአምር ምን እንማራለን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 83 ገጽ 194-ገጽ 195 አን. 1
ሐዋርያቱ ለሕዝቡ ምግብ ሲያከፋፍሉ

ትምህርት 83

ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን መገበ

ጊዜው 32 ዓ.ም. ሲሆን የፋሲካ በዓል የሚከበርበት ወቅት ተቃርቧል፤ ሐዋርያቱ በተለያዩ ቦታዎች ሲሰብኩ ቆይተው ወደ ኢየሱስ ተመለሱ። በዚህ ጊዜ ሐዋርያቱ በጣም ደክሟቸው ስለነበር እረፍት እንዲያደርጉ ኢየሱስ በጀልባ ወደ ቤተሳይዳ ይዟቸው ሄደ። ሆኖም ጀልባው ባሕሩ ዳር ሲደርስ ኢየሱስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተከትለዋቸው እንደመጡ አየ። ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብቻ መሆን ፈልጎ የነበረ ቢሆንም ሰዎቹን ሲመለከት አዘነላቸው። በመሆኑም የታመሙትን ሰዎች ፈወሰ፤ ከዚያም ያስተምራቸው ጀመር። ኢየሱስ ቀኑን ሙሉ ስለ አምላክ መንግሥት ሲያስተምራቸው ቆየ። ቀኑ እየመሸ ሲሄድ ሐዋርያቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው እንዲህ አሉት፦ ‘ሰዎቹ ርቧቸዋል። ሄደው የሚበሉት ምግብ ቢገዙ አይሻልም?’

አንድ ልጅ ለኢየሱስ ዳቦና ዓሣ የያዘ ቅርጫት ሲሰጠው

ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ ‘መሄድ አያስፈልጋቸውም። የሚበሉት ነገር ስጧቸው።’ ሐዋርያቱም ‘ሄደን ለእነሱ የሚሆን ዳቦ እንድንገዛ ትፈልጋለህ?’ ብለው ጠየቁት። ከሐዋርያቱ አንዱ የሆነው ፊልጶስም ‘የ200 ዲናር ዳቦ ብንገዛ እንኳ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ አይበቃም’ አለ።

ኢየሱስ ‘እናንተ ምን የሚበላ ነገር ይዛችኋል?’ ብሎ ጠየቃቸው። እንድርያስም ‘አምስት ዳቦና ሁለት ትናንሽ ዓሣ አለን። ይህ ግን በምንም ዓይነት ለሕዝቡ ሊበቃ አይችልም’ አለ። ኢየሱስም ‘ዳቦውንና ዓሣውን አምጡልኝ’ አላቸው። ከዚያም ሰዎቹ ሣሩ ላይ ሃምሳ ሃምሳና መቶ መቶ እየሆኑ በቡድን እንዲቀመጡ ነገራቸው። ኢየሱስ ዳቦውንና ዓሣውን ይዞ ወደ ሰማይ ቀና በማለት ጸለየ። ከዚያም ምግቡን ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፤ እነሱም ለሕዝቡ አከፋፈሉ። በቦታው የነበሩት 5,000 ወንዶች እንዲሁም ብዙ ሴቶችና ልጆች እስኪጠግቡ ድረስ በሉ። በኋላም ሐዋርያቱ የተረፈው ምግብ እንዳይባክን ሰበሰቡት። የተረፈው ምግብ 12 ቅርጫት ሙሉ ሆነ! ይህ በጣም አስገራሚ የሆነ ተአምር ነው!

ሕዝቡ በጣም ስለተደነቁ ኢየሱስን ንጉሣቸው ሊያደርጉት ፈለጉ። ሆኖም ኢየሱስ፣ ይሖዋ እሱን የሚያነግሥበት ጊዜ እንዳልደረሰ ያውቅ ነበር። በመሆኑም ሰዎቹ ወደየአካባቢያቸው እንዲሄዱ ካደረገ በኋላ ሐዋርያቱን የገሊላን ባሕር አቋርጠው እንዲሻገሩ ነገራቸው። ስለዚህ እነሱ በጀልባ ተጓዙ፤ ኢየሱስ ደግሞ ብቻውን ወደ ተራራ ወጣ። ለምን? ወደ አባቱ መጸለይ ስለፈለገ ነው። ኢየሱስ ምንም ያህል ሥራ ቢበዛበት ለጸሎት ጊዜ ይመድብ ነበር።

“ለሚጠፋ ምግብ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ዘላቂ ለሆነውና የዘላለም ሕይወት ለሚያስገኘው ምግብ ሥሩ።”—ዮሐንስ 6:27

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ለሰዎች እንደሚያስብ ያሳየው እንዴት ነው? ይህስ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?

ማቴዎስ 14:14-22፤ ማርቆስ 6:30-44፤ ሉቃስ 9:10-17፤ ዮሐንስ 6:1-15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ