የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 84 ገጽ 196-ገጽ 197 አን. 4
  • ኢየሱስ በውኃ ላይ ሄደ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ በውኃ ላይ ሄደ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ሊጠብቀን ይችላል
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አሰኘው
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • የተፈጥሮ ኃይሎችን መቆጣጠር የሚችል ገዢ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • አንዲት መርከብ በአንድ ደሴት አጠገብ ተሰበረች
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 84 ገጽ 196-ገጽ 197 አን. 4
ኢየሱስ በውኃ ላይ እየተራመደ ጴጥሮስን ወደ እሱ እንዲመጣ ሲነግረው

ትምህርት 84

ኢየሱስ በውኃ ላይ ሄደ

ኢየሱስ የታመሙ ሰዎችን ከመፈወስና የሞቱ ሰዎችን ከማስነሳት በተጨማሪ ነፋስንና ዝናብን የመቆጣጠር ችሎታም ነበረው። ኢየሱስ በተራራ ላይ ሲጸልይ ቆይቶ ወደ ታች ወደ ገሊላ ባሕር ሲመለከት አውሎ ነፋስ ባሕሩን ሲያናውጠው አየ። ሐዋርያቱ ከነፋሱ በተቃራኒ አቅጣጫ ጀልባውን ለመቅዘፍ እየታገሉ ነበር። ኢየሱስ ከተራራው ወርዶ በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባው መጣ። ሐዋርያቱ በውኃው ላይ የሚሄድ ሰው ሲያዩ በጣም ደነገጡ። ኢየሱስ ግን ‘እኔ ነኝ። አትፍሩ’ አላቸው።

ኢየሱስ በውኃ ላይ እየተራመደ ጴጥሮስን ወደ እሱ እንዲመጣ ሲነግረው

ከዚያም ጴጥሮስ ‘ጌታ ሆይ፣ በእርግጥ አንተ ከሆንክ በውኃው ላይ እየተራመድኩ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ’ አለው። ኢየሱስም ጴጥሮስን ‘ወደ እኔ ና!’ አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ላይ ወርዶ በአውሎ ነፋሱ መሃል በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ ኢየሱስ ሄደ። ሆኖም ወደ ኢየሱስ እየቀረበ ሲመጣ አውሎ ነፋሱን አየና ፈራ። ከዚያም መስመጥ ጀመረ። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ ‘ጌታ ሆይ፣ አድነኝ!’ ብሎ ጮኸ። ኢየሱስም እጁን ያዘውና እንዲህ አለው፦ “አንተ እምነት የጎደለህ! ለምን ተጠራጠርክ?”

ኢየሱስና ጴጥሮስ ጀልባው ላይ ወጡ፤ አውሎ ነፋሱም ወዲያው ጸጥ አለ። ሐዋርያቱ ምን ተሰምቷቸው ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላለህ? ኢየሱስን “አንተ በእርግጥ የአምላክ ልጅ ነህ” አሉት።

ኢየሱስ የአየር ሁኔታን መቆጣጠር እንደሚችል ያሳየው በዚህ ጊዜ ብቻ አልነበረም። በአንድ ወቅት ኢየሱስና ሐዋርያቱ ወደ ባሕሩ ማዶ በጀልባ እየተሻገሩ ሳሉ ኢየሱስ በጀልባው የኋለኛ ክፍል ተኝቶ ነበር። እሱ ተኝቶ ሳለ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተነሳ። ማዕበሉም ከጀልባው ጋር እየተላተመ ወደ ውስጥ ይገባ ጀመር፤ በመሆኑም ጀልባው በውኃ ተሞላ። ሐዋርያቱም ኢየሱስን ቀስቅሰው ከፍ ባለ ድምፅ ‘መምህር፣ መሞታችን ነው! እርዳን!’ አሉት። ኢየሱስም ተነስቶ ባሕሩን “ጸጥ በል!” አለው። ወዲያውኑም ነፋሱና ባሕሩ ጸጥ አለ። ከዚያም ኢየሱስ ሐዋርያቱን ‘እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?’ አላቸው። እነሱም እርስ በርሳቸው “ነፋስና ባሕር እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ። ሐዋርያቱ ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ እስከተማመኑ ድረስ ምንም ነገር መፍራት እንደማያስፈልጋቸው ተገነዘቡ።

“በሕያዋን ምድር የይሖዋን ጥሩነት አያለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር!”—መዝሙር 27:13

ጥያቄ፦ ጴጥሮስ መስመጥ የጀመረው ለምንድን ነው? ሐዋርያቱ ምን ተማሩ?

ማቴዎስ 8:23-27፤ 14:23-34፤ ማርቆስ 4:35-41፤ 6:45-52፤ ሉቃስ 8:22-25፤ ዮሐንስ 6:16-21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ