የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 85 ገጽ 198-ገጽ 199 አን. 1
  • ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድን ዓይነ ስውር ፈወሰ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድን ዓይነ ስውር ፈወሰ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፈሪሳውያን ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው በጥያቄ አፋጠጡት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ፈሪሳውያን ሆነ ብለው ለማመን አልፈለጉም
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ዓይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ሰው መፈወስ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ሲወለድ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነን ሰው ፈወሰ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 85 ገጽ 198-ገጽ 199 አን. 1
ፈሪሳውያን ዓይነ ስውር የነበረውን ሰው ሲጠይቁት

ትምህርት 85

ኢየሱስ በሰንበት ቀን አንድን ዓይነ ስውር ፈወሰ

ፈሪሳውያን ኢየሱስን ይጠሉት ስለነበር እሱን የሚያስሩበት ምክንያት ይፈልጉ ነበር። ስለዚህ በሰንበት ቀን የታመሙ ሰዎችን መፈወስ እንደሌለበት ተናገሩ፤ ምክንያቱም ሰንበት ለአይሁዳውያን የእረፍት ቀን ነበር። ኢየሱስ፣ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዓይነ ስውር የሆነ አንድ ሰው በሰንበት ቀን መንገድ ላይ ሲለምን አየ። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን ‘የአምላክ ኃይል ይህን ሰው እንዴት እንደሚረዳው እዩ’ አላቸው። ኢየሱስ ምራቁን ተፍቶ ከአፈር ጋር ደባለቀውና የሰውየውን ዓይን ቀባው። ከዚያም ኢየሱስ ሰውየውን ‘ወደ ሰሊሆም ገንዳ ሄደህ ዓይንህን ታጠብ’ አለው። ሰውየውም ኢየሱስ እንዳለው አደረገ፤ ከዚያም በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት ቻለ።

ሰዎች የተፈወሰውን ሰው ሲያዩት በጣም ደነገጡ። እንዲህ አሉ፦ ‘ይህ ሰው ተቀምጦ ይለምን የነበረው ሰው ነው ወይስ እሱን የሚመስል ሌላ ሰው?’ ሰውየውም ‘እኔው ነኝ’ አለ። ሰዎቹም ‘ታዲያ እንዴት ማየት ቻልክ?’ አሉት። እሱም የተፈጠረውን ነገር ሲነግራቸው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት።

ሰውየው ፈሪሳውያኑን እንዲህ አላቸው፦ ‘ኢየሱስ ዓይኔ ላይ ጭቃ ከቀባ በኋላ ሄጄ እንድታጠብ ነገረኝ። እኔም ሄጄ ታጠብኩ፤ ከዚያም ማየት ቻልኩ።’ ፈሪሳውያኑም ‘ኢየሱስ በሰንበት ሰዎችን የሚፈውስ ከሆነ የሚፈውሰው በአምላክ ኃይል ሊሆን አይችልም’ አሉ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ ‘በአምላክ ኃይል ባይሆንማ የታመሙ ሰዎችን መፈወስ አይችልም ነበር’ አሉ።

ፈሪሳውያን የሰውየውን ወላጆች ጠርተው ‘ልጃችሁ ማየት የቻለው እንዴት ነው?’ ብለው ጠየቋቸው። ወላጆቹ መልስ ለመስጠት ፈሩ፤ ምክንያቱም ፈሪሳውያን በኢየሱስ የሚያምን ሰው ሁሉ ከምኩራብ እንዲባረር ወስነው ነበር። ስለዚህ ‘እኛ አናውቅም። እናንተ ራሳችሁ ጠይቁት’ አሉ። ፈሪሳውያኑ ሰውየውን በድጋሚ ጠየቁት፤ ከዚያም ሰውየው ‘የማውቀውን ነገር በሙሉ ነግሬያችኋለሁ። ደጋግማችሁ የምትጠይቁኝ ለምንድን ነው?’ አላቸው። ፈሪሳውያኑ በጣም ስለተናደዱ ሰውየውን አባረሩት።

ኢየሱስ ሰውየውን ፈልጎ አገኘውና ‘በመሲሑ ላይ እምነት አለህ?’ በማለት ጠየቀው። ሰውየውም ‘መሲሑ ማን እንደሆነ ባውቅ ኖሮ አምንበት ነበር’ አለ። ኢየሱስም ‘መሲሑ እኔ ነኝ’ አለው። ኢየሱስ የሰውየውን ዓይን መፈወስ ብቻ ሳይሆን በመሲሑ ላይ እምነት እንዲኖረውም ረድቶታል። ኢየሱስ ይህን ማድረጉ ምን ያህል ደግና አሳቢ እንደሆነ የሚያሳይ አይደለም?

“እናንተ ቅዱሳን መጻሕፍትንም ሆነ የአምላክን ኃይል ስለማታውቁ ተሳስታችኋል።”—ማቴዎስ 22:29

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ዓይነ ስውሩን ሰው የረዳው እንዴት ነው? ፈሪሳውያን ኢየሱስን የጠሉት ለምን ነበር?

ዮሐንስ 9:1-41

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ