የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 91 ገጽ 212-ገጽ 213 አን. 1
  • ኢየሱስ ከሞት ተነሳ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ከሞት ተነሳ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ ልጁን አልረሳውም
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • ኢየሱስ ተነሳ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ባዶ መቃብር—ኢየሱስ ሕያው ሆነ!
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ኢየሱስ ሕያው ሆነ!
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 91 ገጽ 212-ገጽ 213 አን. 1
ሴቶቹ የኢየሱስ መቃብር ባዶ መሆኑን አይተው ሲደነግጡ

ትምህርት 91

ኢየሱስ ከሞት ተነሳ

ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሀብታም ሰው ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን አስከሬን ከእንጨቱ ላይ አውርዶ ለመውሰድ ጠየቀ። ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ በጨርቅ ከጠቀለለው በኋላ በአዲስ መቃብር ውስጥ አስቀመጠው። ከዚያም መቃብሩ በትልቅ ድንጋይ እንዲዘጋ አደረገ። የካህናት አለቆቹ ጲላጦስን ‘አንዳንድ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው አስከሬኑን በመውሰድ ኢየሱስ ከሞት ተነስቷል ብለው ሊያስወሩ ይችላሉ’ አሉት። ስለዚህ ጲላጦስ ‘መቃብሩን አሽጉት፤ ከዚያም ጠባቂዎችን አቁሙ’ አላቸው።

ከሦስት ቀን በኋላ፣ አንዳንድ ሴቶች በጠዋት ወደ መቃብሩ ሲሄዱ ድንጋዩ ከመቃብሩ መግቢያ ላይ ተንከባሎ አገኙት። በዚያ የነበረ አንድ መልአክ ሴቶቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘አትፍሩ። ኢየሱስ ተነስቷል። ሂዱና ለደቀ መዛሙርቱ ወደ ገሊላ ሄደው ኢየሱስን እንዲያገኙት ንገሯቸው።’

መግደላዊቷ ማርያም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ለማግኘት ፈጥና ሄደች። ባገኘቻቸውም ጊዜ ‘የኢየሱስ አስከሬን ተወስዷል!’ ብላ ነገረቻቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ እየሮጡ ወደ መቃብሩ ሄዱ። ከዚያም መቃብሩ ባዶ መሆኑን ሲያዩ ወደ ቤታቸው ተመለሱ።

ማርያም ወደ መቃብሩ ስትመለስ በመቃብሩ ውስጥ ሁለት መላእክት አየች፤ እነሱንም ‘ጌታዬን ወዴት እንደወሰዱት አላውቅም’ አለቻቸው። ከዚያም አንድ ሰው አየች፤ ይህ ሰው አትክልተኛው ስለመሰላት ‘እባክህ ጌታዬን ወዴት እንደወሰድከው ንገረኝ’ አለችው። ሆኖም ሰውየው “ማርያም!” ብሎ ሲጠራት ኢየሱስ መሆኑን አወቀች። ከዚያም “መምህር!” ብላ ጮኸችና አቀፈችው። ኢየሱስም ‘ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔን እንዳየሽኝ ንገሪያቸው’ አላት። ማርያምም ወዲያውኑ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሄዳ ኢየሱስን እንዳየችው ነገረቻቸው።

በዚያው ቀን ሁለት ደቀ መዛሙርት ከኢየሩሳሌም ወደ ኤማሁስ እየተጓዙ ነበር። በመንገድ ላይ ሳሉ አንድ ሰው አብሯቸው መሄድ ጀመረ፤ ከዚያም ስለ ምን እያወሩ እንደሆነ ጠየቃቸው። እነሱም እንዲህ አሉት፦ ‘አልሰማህም እንዴ? ከሦስት ቀን በፊት የካህናት አለቆች ኢየሱስን አስገድለውት ነበር። አሁን ደግሞ አንዳንድ ሴቶች ኢየሱስ ተነስቷል እያሉ ነው!’ ሰውየውም ‘ነቢያት የተናገሩትን ነገር አታምኑም? ክርስቶስ እንደሚሞት ከዚያም እንደሚነሳ ተናግረዋል’ አላቸው። ከዚያም ቅዱሳን መጻሕፍት ምን እንደሚሉ አብራራላቸው። ደቀ መዛሙርቱ ኤማሁስ ሲደርሱ አብሯቸው እንዲያድር ጠየቁት። ራት ለመብላት ተቀምጠው ሳሉ ዳቦውን አንስቶ ሲጸልይ ደቀ መዛሙርቱ ይህ ሰው ኢየሱስ መሆኑን ተገነዘቡ። ከዚያም ኢየሱስ ተሰወረባቸው።

ሁለቱ ደቀ መዛሙርት በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፤ በዚያም ሐዋርያቱን አንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው አገኟቸውና ያጋጠማቸውን ነገር ነገሯቸው። ቤቱ ውስጥ እንዳሉ ኢየሱስ ለሁሉም ተገለጠላቸው። በመጀመሪያ ሐዋርያቱ ኢየሱስ መሆኑን አላመኑም ነበር። በኋላ ግን ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ ‘እጆቼን ተመልከቱ፤ ዳስሳችሁ እዩ። ክርስቶስ ከሞት እንደሚነሳ አስቀድሞ ተጽፏል።’

“እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”—ዮሐንስ 14:6

ጥያቄ፦ ሴቶቹ ወደ ኢየሱስ መቃብር ሲሄዱ ምን ገጠማቸው? ወደ ኤማሁስ እየሄዱ የነበሩት ደቀ መዛሙርት ምን ሁኔታ አጋጠማቸው?

ማቴዎስ 27:57–28:10፤ ማርቆስ 15:42–16:8፤ ሉቃስ 23:50–24:43፤ ዮሐንስ 19:38–20:23

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ