የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 92 ገጽ 214-ገጽ 215 አን. 1
  • ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በድጋሚ ታየ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በድጋሚ ታየ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በገሊላ ባሕር ዳርቻ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • በገሊላ ባሕር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • በገሊላ ባሕር
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • የሰዎች አጥማጅ ሆኖ ማገልገል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 92 ገጽ 214-ገጽ 215 አን. 1
ኢየሱስ ዓሣ እየጠበሰ ደቀ መዛሙርቱን ሲያነጋግራቸው

ትምህርት 92

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በድጋሚ ታየ

ኢየሱስ ለሐዋርያቱ ከተገለጠ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ጴጥሮስ ወደ ገሊላ ባሕር ሄዶ ዓሣ ለማጥመድ አሰበ። ቶማስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና አንዳንድ ሌሎች ደቀ መዛሙርትም አብረውት ሄዱ። ሌሊቱን ሙሉ ዓሣ ለማጥመድ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።

በቀጣዩ ቀን ጠዋት ላይ አንድ ሰው በባሕሩ ዳርቻ ቆሞ አዩ። እሱም ‘ዓሣ ያዛችሁ?’ ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም “አልያዝንም!” አሉት። ከዚያም ሰውየው “መረቡን ከጀልባዋ በስተ ቀኝ ጣሉት” አላቸው። ልክ እሱ እንደነገራቸው ሲያደርጉ መረቡ ብዙ ዓሣ ከመያዙ የተነሳ ሊጎትቱት አልቻሉም። በዚህ ጊዜ ዮሐንስ ሰውየው ኢየሱስ መሆኑን አወቀ፤ ከዚያም “ጌታ እኮ ነው!” አለ። ጴጥሮስ ወዲያውኑ ወደ ውኃው ዘሎ በመግባት እየዋኘ ወደ ባሕሩ ዳር ሄደ። ሌሎቹ ደቀ መዛሙርትም በጀልባ ተከተሉት።

ወደ ባሕሩ ዳርቻ እንደደረሱ ዳቦና በእሳት ላይ እየተጠበሰ ያለ ዓሣ አዩ። ኢየሱስም ከያዙት ዓሣ ላይ የተወሰነውን እንዲያመጡ ነገራቸው። ከዚያም ‘ኑ፣ ቁርስ ብሉ’ አላቸው።

ጴጥሮስ በባሕር ዳርቻ ወዳለው ወደ ኢየሱስ ሲቃረብ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት በጀልባ እየተከተሉት ነው

ቁርስ በልተው ከጨረሱ በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን ‘ዓሣ ከማጥመድ ሥራህ የበለጠ ትወደኛለህ?’ አለው። ጴጥሮስም “አዎ፣ ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” አለው። ከዚያም ኢየሱስ “ጠቦቶቼን መግብ” አለው። ኢየሱስ በድጋሚ ‘ጴጥሮስ፣ ትወደኛለህ?’ ብሎ ጠየቀው። ጴጥሮስም “ጌታ ሆይ፣ በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ” ብሎ መለሰለት። ኢየሱስም “ግልገሎቼን ጠብቅ” አለው። ኢየሱስ ጴጥሮስን ለሦስተኛ ጊዜ ጠየቀው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በጣም አዘነ። ከዚያም ‘ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉንም ነገር ታውቃለህ። በጣም እንደምወድህ ታውቃለህ’ አለው። ኢየሱስም “ግልገሎቼን መግብ” አለው። ይህን ካለ በኋላም ለጴጥሮስ “እኔን መከተልህን ቀጥል” የሚል ምክር ሰጠው።

“[ኢየሱስም] ‘ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰው አጥማጆች አደርጋችኋለሁ’ አላቸው። እነሱም ወዲያውኑ መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት።”—ማቴዎስ 4:19, 20

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ምን ተአምር ፈጸመ? ኢየሱስ ጴጥሮስን “ትወደኛለህ?” ብሎ ሦስት ጊዜ የጠየቀው ለምን ይመስልሃል?

ዮሐንስ 21:1-19, 25፤ የሐዋርያት ሥራ 1:1-3

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ