የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 93 ገጽ 216-ገጽ 217 አን. 5
  • ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከጴንጤቆስጤ በፊት በርካቶች አዩት
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ለመጨረሻ ጊዜ ለደቀ መዛሙርቱ የታየባቸው ጊዜያትና የ33 እዘአ የጴንጤቆስጤ ዕለት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • በመጨረሻ የተገለጠባቸው ጊዜያትና በ33 እንደ ዘመናችን አቆጣጠር የዋለው ጰንጠቆስጤ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • በደብረ ዘይት ተራራ ላይ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 93 ገጽ 216-ገጽ 217 አን. 5
ሐዋርያቱ እያዩት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲወጣ

ትምህርት 93

ኢየሱስ ወደ ሰማይ ተመለሰ

ኢየሱስ በገሊላ ከተከታዮቹ ጋር ተገናኘ። ከዚያም የሚከተለውን በጣም አስፈላጊ የሆነ ትእዛዝ ሰጣቸው፦ ‘ሂዱና ከሁሉም አገሮች ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ። ያስተማርኳችሁን ነገሮች አስተምሯቸው፤ እንዲሁም አጥምቋቸው።’ ቀጥሎም ‘ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ’ በማለት ቃል ገባላቸው።

ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ በነበሩት 40 ቀናት ውስጥ በገሊላና በኢየሩሳሌም በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደቀ መዛሙርቱ ታየ። በዚህ ወቅት አስፈላጊ የሆነ ትምህርት ሰጣቸው እንዲሁም ብዙ ተአምራትን ፈጸመ። ከዚያም በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ ከሐዋርያቱ ጋር ተገናኘ።

ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ሐዋርያቱን እንዲህ ብሏቸው ነበር፦ ‘ከዚህች ከተማ አትውጡ። አባቴ ቃል የገባው ነገር እስኪፈጸም ድረስ እዚሁ ጠብቁ።’ ሐዋርያቱ ግን ኢየሱስ ምን ማለቱ እንደሆነ አልገባቸውም ነበር። ስለዚህ ‘የእስራኤል ንጉሥ የምትሆነው አሁን ነው?’ ብለው ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ ‘ይሖዋ የወሰነው ጊዜ ገና አልደረሰም። በቅርቡ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ይወርዳል። በዚያን ጊዜ ኃይል ታገኛላችሁ፤ ምሥክሮቼም ትሆናላችሁ። ሂዱና በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ በሰማርያ እንዲሁም እስከ ምድር ዳር ድረስ ስበኩ።’

ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሰማይ ወጣ፤ ደመናም ሸፈነው። ደቀ መዛሙርቱ ወደ ላይ ማየታቸውን ቀጠሉ፤ እሱ ግን ተሰወረ።

ደቀ መዛሙርቱ ከደብረ ዘይት ተራራ ተነስተው ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ። በዚያም ሰገነት ላይ በሚገኝ አንድ ክፍል ውስጥ አዘውትረው ይሰበሰቡና ይጸልዩ ነበር። ኢየሱስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተጨማሪ መመሪያ እስኪሰጣቸው ድረስ ሲጠብቁ ቆዩ።

“ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”—ማቴዎስ 24:14

ጥያቄ፦ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ምን ትእዛዝ ሰጣቸው? በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ምን ነገር ተፈጸመ?

ማቴዎስ 28:16-20፤ ሉቃስ 24:49-53፤ ዮሐንስ 20:30, 31፤ የሐዋርያት ሥራ 1:2-14፤ 1 ቆሮንቶስ 15:3-6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ