የክፍል 6 ማስተዋወቂያ
እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ከገቡ በኋላ የማደሪያው ድንኳን የእውነተኛው አምልኮ ማዕከል ሆኖ ነበር። ካህናት ሕጉን ያስተምሩ፣ መሳፍንት ደግሞ ሕዝቡን ይመሩ ነበር። ይህ ክፍል አንድ ሰው የሚወስነው ውሳኔና የሚያደርገው ነገር በሌሎች ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ያብራራል። እያንዳንዱ እስራኤላዊ በግለሰብ ደረጃ ለይሖዋም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ታማኝ መሆን ይጠበቅበት ነበር። ዲቦራ፣ ናኦሚ፣ ኢያሱ፣ ሐና፣ የዮፍታሔ ልጅና ሳሙኤል በሕዝባቸው ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ አሳድረው እንደነበር አብራራ። እንደ ረዓብ፣ ሩት፣ ኢያዔልና ገባዖናውያን ያሉ እስራኤላዊ ያልሆኑ ሰዎችም እንኳ አምላክ ከእስራኤላውያን ጋር እንደሆነ በማወቃቸው ከእነሱ ጎን ለመቆም እንደወሰኑ ጎላ አድርገህ ግለጽ።