መዝሙር 17
“እፈልጋለሁ”
በወረቀት የሚታተመው
(ሉቃስ 5:13)
1. ደግ፣ ሩኅሩኅ አሳቢ ነበር፣
ክርስቶስ ሲኖር በምድር።
ያስደስተው ነበር
ሰዎችን መርዳት፤
ለሌሎች ጊዜውን መስጠት።
አልረሳም ችግረኞችን፤
ፈውሷል የታመሙትን።
ተል’ኮውን ተወጣ በደስታ፤
“’ፈልጋለሁ” ብሏል ጌታ።
2. ክርስቶስ ነው ምሳሌያችን፤
ፈለጉን ’ንከተላለን።
እውነትን ስንሰብክ
’ንሁን አፍቃሪ፣
ደግና ሰውን አክባሪ።
ወንድሞች ሲቸግራቸው
በምንችለው እንርዳቸው።
አጋር፣ ወላጅ ያጡ ሲቸገሩ
‘መርዳት ’ፈልጋለሁ’ በሉ።