መዝሙር 93
ለስብሰባ ስንገናኝ በረከትህ አይለየን
በወረቀት የሚታተመው
1. ተሰብስበናል በፊትህ፤
አባት ሆይ፣ ባርከን ’ባክህ።
ለዚህ ዝግጅት ተመስገን፤
መንፈስህ አይለየን።
2. አምልኳችን ንጹሕ ይሁን፤
አስተምረን ቃልህን።
ልባችን ፍቅር ይሙላበት፤
አሠልጥነን ለስብከት።
3. ስብሰባችንን ባርክልን፤
ሰላም፣ አንድነት ስጠን።
ቃላችንና ሥራችን፣
ያስከብረው ስምህን።
(በተጨማሪም መዝ. 22:22፤ 34:3ን እና ኢሳ. 50:4ን ተመልከት።)