መዝሙር 102
‘ደካማ የሆኑትን እርዱ’
በወረቀት የሚታተመው
1. ብዙ ነው ድክመታችን፣
የሁላችንም።
አምላክ ግን ይወደናል፤
ያስብልናል።
እሱ መሐሪ ነው፤
ፍቅሩ ወደር የለው።
እኛም ለተጨነቁት
ፍቅር ይኑረን።
2. ጠንካራ ’ሚመስል ሰው
ሊዝል ይችላል፤
ስናበረታታው ግን
በ’ምነት ይጸናል።
አምላክ ያጸናዋል፤
ብርታት ይሰጠዋል።
እኛም እንዘንለት፤
እናስብለት።
3. ደካሞችን ከመንቀፍ
እናግዛቸው።
ደግነት በማሳየት
እናበርታቸው።
ሳንሰለች በመርዳት፣
ብንሆናቸው ብርታት፣
ደስተኞች ይሆናሉ፤
እፎይ ይላሉ።
(በተጨማሪም ኢሳ. 35:3, 4ን፣ 2 ቆሮ. 11:29ን እና ገላ. 6:2ን ተመልከት።)