መዝሙር 103
እረኞች—ስጦታ የሆኑ ወንዶች
በወረቀት የሚታተመው
(ኤፌሶን 4:8)
1. አምላካችን በደግነቱ
እረኞች ሰጥቶናል፤
ምሳሌ ሆነው በማገልገል
መንገድ ይመሩናል።
(አዝማች)
አምላክ ሰጥቶናል ታማኝ ወንዶች፣
እውነተኛ እረኞች።
ለመንጋው ’ሚጨነቁ ናቸው፤
ምንጊዜም አድንቋቸው።
2. በርኅራኄ ይይዙናል፣
በፍቅር በመምራት።
ስንጎዳ ይጠግኑናል፣
በቃል በማጽናናት።
(አዝማች)
አምላክ ሰጥቶናል ታማኝ ወንዶች፣
እውነተኛ እረኞች።
ለመንጋው ’ሚጨነቁ ናቸው፤
ምንጊዜም አድንቋቸው።
3. ከአምላክ መንገድ እንዳንወጣ፣
ምክር ይሰጡናል።
ሁሌ እንድናገለግለው፣
ያበረታቱናል።
(አዝማች)
አምላክ ሰጥቶናል ታማኝ ወንዶች፣
እውነተኛ እረኞች።
ለመንጋው ’ሚጨነቁ ናቸው፤
ምንጊዜም አድንቋቸው።
(በተጨማሪም ኢሳ. 32:1, 2ን፣ ኤር. 3:15ን፣ ዮሐ. 21:15-17ን እና ሥራ 20:28ን ተመልከት።)