መዝሙር 104
የአምላክ ስጦታ የሆነው መንፈስ ቅዱስ
በወረቀት የሚታተመው
1. ልዑሉ አምላክ፣ መሐሪው አባት፣
ከልባችን ይበልጥ ታላቅ ነህ።
ሸክማችንን ቀላል አ’ርግልን፤
’ባክህ ስጠን አጽናኝ መንፈስህን።
2. ልናንጸባርቅ አንችል ክብርህን፤
ብዙ ጊዜ እንስታለን።
አምላክ ሆይ፣ እንማጸንሃለን፣
መንፈስህ በየቀኑ ’ንዲመራን።
3. ስንዝል፣ ስንደክም፣ ተስፋ ስንቆርጥ፣
መንፈስህ ነው እኛን ’ሚያድሰን።
እንደ ንስር መብረር እንድንችል፣
ኃያል ቅዱስ መንፈስህን ስጠን።