የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ልብ ብላችሁ አዳምጡ፦
ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው? አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው? (ማቴ. 22:37, 38፤ ማር. 12:30)
ዓለምን እንዳንወድ ምን ሊረዳን ይችላል? (1 ዮሐ. 2:15-17)
ሰዎች ‘የይሖዋን ስም እንዲወዱ’ ማስተማር የምንችለው እንዴት ነው? (ኢሳ. 56:6, 7)
ግብዝነት የሌለበት የወንድማማች ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? (1 ዮሐ. 4:21)
ወላጆች፣ ልጆቻቸው ይሖዋን እንዲወዱ ማስተማር የሚችሉት እንዴት ነው? (ዘዳ. 6:4-9)
ይሖዋ የቅርብ ወዳጃችሁ መሆኑን በግልጽ ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው? (1 ዮሐ. 5:3)
ለይሖዋ ያለንን ፍቅር ይዘን መቀጠል ወይም ማቀጣጠል የምንችለው እንዴት ነው? (ራእይ 2:4, 5)