ክፍል ሁለት
‘መቅደሴን አርክሰሻል’—ንጹሕ አምልኮ ተበከለ
ፍሬ ሐሳብ፦ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ለመንፈሳዊም ሆነ ለሥነ ምግባራዊ ብክለት ተዳረጉ
ይሖዋ እስራኤላውያን ‘ልዩ ንብረቶቹ’ ስለሆኑ ይወዳቸውና ይንከባከባቸው ነበር። (ዘፀ. 19:5) እነሱ ግን ስሙ በተጠራበት ቤተ መቅደስ ውስጥ የሐሰት አማልክትን በማምለክ ውለታ ቢስ መሆናቸውን አሳዩ። የይሖዋን ልብ በእጅጉ ያሳዘኑ ከመሆኑም ሌላ ስሙን አሰድበዋል። እስራኤላውያን እንዲህ ያለ ያዘቀጠ ድርጊት ሊፈጽሙ የቻሉት ለምንድን ነው? ሕዝቅኤል ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት ከተናገረው ትንቢት ምን እንማራለን? እስራኤላውያን በዙሪያቸው ካሉት ብሔራት ጋር ከነበራቸው ግንኙነትስ ምን ትምህርት እናገኛለን?