የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ልብ ብላችሁ አዳምጡ፦
‘የክርስቶስ ሕግ’ ምንድን ነው? (ገላ. 6:2)
ሰዎች በማያዩን ጊዜም የክርስቶስን ሕግ መፈጸም የምንችለው እንዴት ነው? (1 ቆሮ. 10:31)
በመስክ አገልግሎት ላይ የክርስቶስን ሕግ መፈጸም የምንችለው እንዴት ነው? (ሉቃስ 16:10፤ ማቴ. 22:39፤ ሥራ 20:35)
የክርስቶስን ሕግ ከሙሴ ሕግ የላቀ የሚያደርገው ምንድን ነው? (1 ጴጥ. 2:16)
ባለትዳሮችና ወላጆች በቤተሰባቸው ውስጥ የክርስቶስን ሕግ መፈጸም የሚችሉት እንዴት ነው? (ኤፌ. 5:22, 23, 25፤ ዕብ. 5:13, 14)
በትምህርት ቤት የክርስቶስን ሕግ መፈጸም የምትችሉት እንዴት ነው? (መዝ. 1:1-3፤ ዮሐ. 17:14)
ክርስቶስ እንደወደደን ሌሎችን መውደድ የምንችለው እንዴት ነው? (ገላ. 6:1-5, 10)