መዝሙር 161
ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል
በወረቀት የሚታተመው
1. ልጅህ ላንተ መኖርን መርጦ፣
ሲወጣ ዮርዳኖስ ገብቶ፤
ልቡ ሞላ ፍቅርህን ሰምቶ፤
‘እነሆኝ!’ አለህ ወዶ።
ዓለም እንዲያውቅህ መሠከረ፤
‘ይህ ነው’ አለ ‘አባቴ!’
ኖረልህ ሳይሳሳ ለራሱ፤
እኔም ይህ ነው ስለቴ።
(አዝማች)
ፈቃድህን ታድርግ ነፍሴ፤
መሻቴ ነው፣ ለኔስ ሐሴት።
ላገልግልህ፣ ልኑርልህ፤
ልብህ ይደሰት በኔ።
ፈቃድህን ታድርግ ነፍሴ፤
ደስታዬ ነው፣ ሕግህ ውርሴ።
ፍቅርህ ጠራኝ፣ ፍቅርህ ገዛኝ፤
ያንተው ይሁን ሕይወቴ፣
እስትንፋሴ።
2. እያደር ሲያውቅህ ወዶህ ልቤ፣
በሐሴት ተሞልቷል ውስጤ፤
አውርቼ አልጠግብም ስላንተ፣
ዝም አይልም አንደበቴ።
ካገልጋዮችህ መሃል አ’ርገኝ፤
’ባክህ ስምህን ልጥራ።
እሳላለሁ ሁሉን ልሰጥህ፤
ያንተው አ’ርገኸኝ ልኩራ።
(አዝማች)
ፈቃድህን ታድርግ ነፍሴ፤
መሻቴ ነው፣ ለኔስ ሐሴት።
ላገልግልህ፣ ልኑርልህ፤
ልብህ ይደሰት በኔ።
ፈቃድህን ታድርግ ነፍሴ፤
ደስታዬ ነው፣ ሕግህ ውርሴ።
ፍቅርህ ጠራኝ፣ ፍቅርህ ገዛኝ፤
ያንተው ይሁን ሕይወቴ፣
እስትንፋሴ።
ላንተው ትኑር ነፍሴ።
(በተጨማሪም መዝሙር 40:3, 10ን ተመልከት።)