የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 6
  • ድፍረት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ድፍረት
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ምን አድርጓል?
  • ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
  • ኢየሱስን ምሰል
  • በድፍረት በመስበክ ኢየሱስን ምሰሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • በድፍረት ትሰብካላችሁን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
  • ‘የአምላክን ቃል በድፍረት ተናገሩ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • የአምላክን ቃል በድፍረት መናገራችሁን ቀጥሉ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 6

ውይይት መጀመር

ኢየሱስ ዘኬዎስን ከዛፍ ላይ እንዲወርድ ሲያበረታታው፤ አንዳንዶች በዚህ ተገርመው እያዩት ነው።

ሉቃስ 19:1-7

ምዕራፍ 6

ድፍረት

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “የአምላክን ምሥራች ለእናንተ ለመንገር በአምላካችን እርዳታ እንደ ምንም ብለን ድፍረት አገኘን።”—1 ተሰ. 2:2

ኢየሱስ ምን አድርጓል?

ኢየሱስ ዘኬዎስን ከዛፍ ላይ እንዲወርድ ሲያበረታታው፤ አንዳንዶች በዚህ ተገርመው እያዩት ነው።

ቪዲዮ፦ ኢየሱስ ለዘኬዎስ ሰበከ

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም ሉቃስ 19:1-7ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. አንዳንድ ሰዎች ከዘኬዎስ ጋር መሆን የማይፈልጉት ለምን ሊሆን ይችላል?

  2. ለ. ኢየሱስ ግን ለዚህ ሰው ምሥራቹን እንዲሰብክ ያነሳሳው ምንድን ነው?

ከኢየሱስ ምን እንማራለን?

2. የመንግሥቱን መልእክት ሳናዳላ ለሁሉም ሰው ለመስበክ ድፍረት ያስፈልገናል።

ኢየሱስን ምሰል

3. የይሖዋን እርዳታ ፈልግ። ኢየሱስ ለመስበክ ኃይል ያገኘው ከአምላክ መንፈስ ነው፤ የአምላክ መንፈስ ለአንተም ኃይል ሊሰጥህ ይችላል። (ማቴ. 10:19, 20፤ ሉቃስ 4:18) ለሚያስፈሩህ ሰዎች ለመስበክ ድፍረት እንዲሰጥህ ይሖዋን ጠይቀው።—ሥራ 4:29

4. ከውጭ አይተህ አትፍረድ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎችን ማነጋገር የሚያስፈራን በውጫዊ ገጽታቸው፣ በኑሮ ደረጃቸው፣ በአኗኗር ዘይቤያቸው ወይም በሃይማኖታቸው የተነሳ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ይህን አስታውስ፦

  1. ሀ. ይሖዋና ኢየሱስ የሰዎችን ልብ ማንበብ ይችላሉ፤ እኛ ግን አንችልም።

  2. ለ. ‘የይሖዋ ምሕረት አይገባውም’ ልንለው የምንችለው ሰው የለም።

5. ድፍረትህ ዘዴኛነትና ጥንቃቄ የታከለበት ይሁን። (ማቴ. 10:16) አተካራ ውስጥ አትግባ። ግለሰቡ ለመስማት ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም ደህንነትህን የሚያሰጋ ነገር እንዳለ ከተሰማህ ውይይቱን በጨዋነት አቋርጥ።—ምሳሌ 17:14

ተጨማሪ ጥቅሶች

ሥራ 4:31፤ ኤፌ. 6:19, 20፤ 2 ጢሞ. 1:7

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ